Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, July 17, 2015

በደቡብ ክልል ጋሙ ጎፋ ዞን አስተዳደር የህወሓት አሻንጉሊት ባለስልጣናት መካከል መከፋፈል ተፈጠረ፡፡

በደቡብ ክልል ጋሙ ጎፋ ዞን አስተዳደር የህወሓት አሻንጉሊት ባለስልጣናት መካከል መከፋፈል ተፈጠረ፡፡

*በደቡብ ክልል ጋሙ ጎፋ ዞን አስተዳደር የህወሓት አሻንጉሊት ባለስልጣናት መካከል መከፋፈል ተፈጠረ፡፡
ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የሚከተለው ከቅኝ ገዥዎች የተወረሰ ህዝብን በመከፋፈል ለረዥም ጊዜ የመግዛት ፀረ ኢትዮጵያዊ አንድነት የሆነ የበሰበሰ አውዳሚ ፖለቲካዊ ቀመር ከጎሳዎች አልፎ በመንደርና ቤተሰብ ውስጥ ገብቶ ስር በመስደድ ላይ ይገኛል፡፡
በመሆኑም በደቡብ ክልል ጋሙ ጎፋ ዞን አስተዳደር የህወሓት አሻንጉሊት ባለስልጣናት መካከል መንደርንና ቋንቋን መሰረት ያደረገ መከፋፈል በመፈጠሩ ጎራ ለይተው እርስበርስ በመሰላለፍ የከረረ ፍልሚያና ሽኩቻ ውስጥ ገብተው ይገኛሉ፡፡
በጋሙ ጎፋ ዞን አስተዳደር ውስጥ ከታቀፉት አምስቱ ጎሳዎች የተውጣጡት የህወሓት አሸርጋጅ የአስተዳደሩ አሻንጉሊት ባለስልጣናት መካከል ከፍተኛ እሰጣገባ የነገሰ ሲሆን በተለይም ደግሞ በጋሙ እና በጎፋ ተወላጅ የህወሓት አገልጋዮች መካከል መከፋፈሉ በማየሉ እርስበርስ መጠላለፉ እና አንዱ ሌላውን ለመጣል የሚደርገው ግብግብ በርትቶ ቀጥሏል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials