Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, July 28, 2015

ኦባማ ጋዜጠኞች መታሰር የለባቸውም አሉ * መሪዎች የስልጣን ጊዜያቸው ሲያልቅ መውረድ አለባቸው ሲሉ አስጠነቀቁ


ኦባማ ጋዜጠኞች መታሰር የለባቸውም አሉ * መሪዎች የስልጣን ጊዜያቸው ሲያልቅ መውረድ አለባቸው ሲሉ አስጠነቀቁ




ከአሰግድ ታመነ

የኢትዮጵያ መንግስት በዲሞክራሲያዊ ምርጫ የመጣ ነው በማለት እጅጉን አስቀይሞን የነበረው ኦባማ ዛሬ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ልዩ ሆኖ ቀረበ።

ኦባማ “ዴሞክራሲ ማለት ፎርማል ምርጫ ማለት ብቻ አይደለም” ሲል አዳራሹ በአንድ እግሩ ቆመ ጭብጨባው ቀለጠ ፉጨቱ አስተጋባ ሁሉም በዚህች ሰበብ ምርጫ እያጭበረበሩ እዴሜ ያራዝሙ ስለነበር እውቅና ያገኙ መሰላቸው የኦባማ ንግግር ግን ባላሰቡት መንገድ ነበር የቀጠለው “ጋዜጠኞች ስራቸውን በመስራታቸው የሚታሰሩ ከሆነ ፣ ወይም መንግስት ሲቪል ሶሳይቲ ላይ በሚወስደው ጥብቅ እርምጃ ንቁ የፖለቲካ ተሳታፊዎች ዛቻ የሚደርስባቸው ከሆነ ያኔ ዴሞክራሲ ስሙ ብቻ ይኖራችኋል ነገር ግን ቁም ነገሩ እና በጣም አስፈላጊ የሆነው ፍሬ ነገር አይኖረውም” በማለት ኩም ሲያደርጋቸው እየደበራቸውም ቢሆን ጭብጨባውን አምበጫረቁት።

እኔ አምናለው ሀገራት የሰጡትን የነፃነት ሙሉ ተስፋ ከፍፃሜ ማድረስ አይችሉም የህዝባቸውን ሙሉ መብት እስካልጠበቁ ድረስ በማለት የህዝብ መብት መከበር እንዳለበት በአንክሮ አሳሰበ።

እኔ አይገባኝም ሰዎች ስልጣን ላይ ረጅም ጊዜ መቆየት ለምን እንደሚፈልጉ በተለይ ብዙ ገንዘብ ካገኙ በኃላ። የአፍሪካ መሪዎች ህገ-መንግስታቸውን ማክበር አለባቸው ፣ የስልጣን ዘመናቸው ሲያልቅ ከስልጣን መውረድ አለባቸው ስልጣን ለማራዘም ሲባል ህገ-መንግስቱን የሚቀያይሩ ከሆነ አለመረጋጋትን ይፈጥራል በማለት የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ለሶስተኛ ጊዜ ለስልጣን መወዳደራቸውን ተከትሎ የተነሳውን ረብሻ በመጥቀስ ማንም ሰው እድሜ ልኩን ፕሬዝዳንት ሆኖ መኖር አይችልም አለ።
እኔ ፕሬዝዳንት መሆኔ ለእኔ ልዩ መብት ነው ከዚህ የተሻለ ኢንተረስቲንግ ስራ አላገኝም ነገር ግን ማንም ሰው ከህግ በላይ መሆን አይችልም ፕሬዝዳንቱም ጭምር ስለዚህ ስለዚህ ለሶስተኛ ጊዜ እንድወዳደር ህጉ ስለማይፈቅድልኝ ስልጣኔን አስረክባለው። እኔ ብቻ ለሀገሬ እማስብ እና መስራት የምችል ብሎ ማሰብ ስህተት ነው በማለት የአፍሪካ መሪዎችን እስከ አፍንጫቸው ነግሯቸው ወረደ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials