በዚህ ወር መጨረሻ የአባታቸውን ሀገር ለሁለት ቀናት ይጎበኛሉ ተብለው የሚጠበቁት ባራክ ኦባማ ወደ ኬኒያ ምድር ሲመጡ በግብረ ሰዶማውያን ጉዳይ ላይ አንዳችም ነገር እንዳይናገሩ በከፍተኛ ሁኔታ ሲያስጠነቅቁ ሰንብተዋል። የተለያዩ እምነት መሪዎችና የፓርላማ አባላት ጭምር ደብዳቤዎችን ለዋይት ሀውስ አስገብተዋል።
የኬኒያ ምክትል ፕሬዚዳንት በበኩላቸው “ይህ የአፍሪካውያን ባህል ካለመሆኑም በላይ ድርጊቱ የሀይማኖታችንን ህግ የሚጥስ ነው።” በማለት ተችተዋል። አንድ የቤተክርስትያን ፓስተር እንዲሁ “እኛ ኦባማና ኦባማን አንፈልግም…ሚሼልና ሚሼልን አንፈልግም። የምንፈልገው ኦባማና ሚሼልን ነው።” በማለት ደብዳቤ መጻፋቸው ተነግሯል። ይሁን እንጂ ከዋሽንግተን የተሰጣቸው ምላሽ ኦባማ ጉዳዩን አንስተው መነጋገራቸው የማይቀር መሆኑን ነው።
ይህም ምላሽ ያስቆጣቸው የናይሮቢ ከተማ ነዋሪዎች ፕሬዚዳንቱ ለሁለት ቀን በሚቆዩበት ጊዜ ራቁታቸውን በመውጣት ይህን አጸያፊ ድርጊት ለመቃወም በመዘጋጀት ላይ ናቸው። “የወንድና የሴትን ተፈጥሯዊ ልዩነት ለኦባማ ማስተማር እንፈልጋለን።” ብለዋል አዘጋጆቹ። ከተፈጥሮ ጋር ልንጋጭ አይገባም ያሉት እነዚሁ ተቃዋሚዎች ኦባማ ይህን ሳይረዳ መኖሩ አስገራሚ ነው በማለት ተችተዋል።
በኛስ ሀገር ይህ ጥያቄ እንዴት ይስተናገድ ይሆን?
የትነበርክ ታደለ
No comments:
Post a Comment