Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, July 18, 2015

አሜሪካኖቹ ዲፕሎማቶች የኦባማ ጉብኝት ለውይይት እንጂ ወንጀለኛን መንግስት ለማጽደቅ እንዳልሆነ አስረዱ

አሜሪካኖቹ ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያ መንግስትን አስጠነቀቁ

አሜሪካኖቹ ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያ መንግስትን አስጠነቀቁ
**የኦባማ ጉብኝት ለውይይት እንጂ ወንጀለኛን መንግስት ለማጽደቅ እንዳልሆነ አስረዱ
** “የተፈቱት የዞን ዘጠኝ ጋዜጠኞች ፓስፖርታቸው እንኳን እንዳልተመለሰ እናውቃለን:: መጀመርያውኑ መታሰር እልነበረባቸውም:: ሲፈቱም አፈታታቸው ሙሉ አይደለም”
ዛሬ እዚህ ዋሺንገተን ዲሲ ላይ ጠንካራ ውይይት ሲካሄድ ነበር:: ውይይቱ የኦባማን የምስራቅ አፍሪካ ጉዞ በተመለከተ ሲሆን : አሜሪካኖቹ መራር መልሶችን ሲመልሱ ተደምጠዋል::
የኦባማ ጉብኝት ለአምባገነኖች ሽፋን መስጠት ሳይሆን ሌሎች በርካታ ዓላማዎች እንዳሉትም አስረድተዋል::
በውይይቱ የዞን ዘጠኝ ጋዜጠኞች አስር ፈጽሞ ያልተገባ መሆኑን ጠቅሰው: ሲፈቱም ሙሉ ነጻነት እንዳልተሰጣቸው ፓስፖርታቸው እንኳን እንዳልተመለሰላቸው አስረድተዋል::ከዚሁም ጋር በተያያዘ ሰሞኑን አቶ ኃይለማርያም ኤርትራን ስለመምታት የተናገሩትን ዛቻ በተመለከተ ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል:: ኢትዮጵያ የኤርትራን ድንበር ጥሳ እንዳትገባና ብትገባ ግን አሜሪካ እንደምታወግዘው ገልጸዋል::
ሌሎችም ሌሎችም ውይይቱ ይህን ይመስል ነበር ::


No comments:

Post a Comment

wanted officials