ኢትዮጵያውያን በጀርመን ኑረምበርግ ፕሬዚዳንት ኦባማን እና ወያኔን የሚቃወም ሰልፍ ኣደረጉ
በባቫርያ ግዛት ኑረምበርግ ከተማ በጁላይ 4,2015 ዓም በተደረገው ይህ ሰላማዊ ሰልፍ ወቅታዊና አነጋጋሪ የሆነውን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የያዙትን እቅድ መለስ ብለው እንዲያጤኑት ለኣምባገነኑ የወያኔ መንግስት ድጋፍ እንዳሰጡ ተጠይቋል።
ባብዛኛው ወጣቶች በታደሙበት በዚህ ሰልፍ ወጣቶቹ ይዘውት የነበረው የ አሜሪካው ፕሬዚዳንት ፎቶ እና ጠንካራ የዲሞክራሲ ተቋማትን እንጂ ጠንካራ አምባገነን ሰዎችን አንፈልግም የሚል መልዕክት ያለበት ጽሁፍ ትልቅ ባነር በጀርመኗ ኑረምብርግ የነበሩ የውጭ ሃገር ዜጎችን ትኩረት ከመሳቡም በላይ በየመንገዱ ተሰላፊዎቹን እያስቆሙ ሲጠይቁ ፎቶም ሲያነሱ ተስተውለዋል። የፕሬዚዳንቱ ፎቶ መነገቡ በተለይም ወቅታዊ ትኩሳት የሆነውን በአሜሪካ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ መፈቀዱን ለማውገዝ የተጠራ ሰልፍ መስሏቸው ለጠየቁ ፈረንጆች የወያኔን አምባገነንነት ፥ሽፍታነት፥አሸባሪነት፥ግብረሰዶማዊነት፥ዘረኝነት ለማስረዳት በር ከፍቶ ያለፈ በመሆኑ ልዩ ሰልፍ ነበር።ጁላይ 4 የተከበረው የ አሜሪካ የነጻነት ቀንም በዚሁ ዕለት ከመሆኑ ጋርም ያገናኙት ነበሩ።
በዋነኛነት በሰልፉ በዘረኛውና በ አምባገነኑ የወያኔ ስርዓት የውሽት ምርጫን ተከትሎ የሰማያዊ እና የመድረክ አባላት ላይ የተፈጸመው ግድያ ተወግዟል፥ በየመን ከታገቱ ጀምሮ የት እንደታሰሩ ወያኔ አላሳውቅ ያለውን የ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አፈና በጥብቅ በመቃወም ብሎም በተለያዩ እስር ቤቶች በግዞት ታስረው በየጊዜው ቶርቸር የሚፈጸምባቸውን ኢትዮጵያውያን የህሊና እስረኞች ባስቸኳይ እንዲፈቱ፥ የጀርመን መንግስት ዘረኛውን ወያኔ እንዳይደግፍ ተጠይቋል።
ሰላማዊ ሰልፉ በከተማዋ ዋና ዋና አውራ ጎዳና ላይ ከ አንድ ሰ አት ያላነሰ የተሽከርካሪ መንገዶች ለሰልፈኞች ሲባል ተዘግቶ በጀርመን ፖሊሶች ድጋፍ ሰጪነት የተደረገ ሲሆን ሰልፉን ያዘጋጀው በጀርመን የ ኢትዮጵያውያን የሲቪክና የፖለቲካ ማህበራት አንድነት ድርጅት ኢፕኮ ነው። ሰልፉ ማብቂያውን ባደረገበት ጎስተን ሆፍ አካባቢ ሰልፈኞቹ በሙሉ ወደ አዳራሽ በመግባት የኢፕኮን ድርጅት በሚመለክትና ትግላችን የእውነት እንጂ የታይታ እንዳይሆን ሰለሚያስፈልገው መስዋዕትነት የሞቀ ውይይት አድርገዋል።
ሪፖርት በአብርሃም

No comments:
Post a Comment