Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, July 27, 2015

‹አልሸባብ ሀብታሙን ቢያገኘው ኖሮ ይገድለው ነበር፡፡” ተማም








”…ፍትሕ ሚኒስቴር በቅርቡ ‹‹በሥነምግባር ችግር›› በሚል የተማምን የጥብቅና ፍቃድ በመሰረዝ ለአንድ ዓመት ከሰባት ወራት እንዳገደው የሚታወቅ ነው፡፡….ተማም ብዙ ጊዜውን በቤቱ በማንበብ ነበር ጊዜውን የሚያሳልፈው፡፡
በጨዋታ መካከል ስለባልደረባችን ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ መታሰር ነገርኩት፡፡ ደነገጠ፡፡ ‹‹አጃኢብ›› አለና ‹‹በምን?›› አለኝ በጣም አዝኖ፡፡ ‹‹የአልሸባብ ህዋስ ነህ፤ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሚገኙበት ስብሰባ ላይ የሽብር ድርጊት ለመፈጸም አሲረሃል›› ተብሎ ተጠርጥሮ መያዙን አስረዳሁት፡፡ ተማምና ሀብታሙ በአካል ይተዋወቃሉ፡፡ ሀብታሙ ከጋዜጠኝነት ሥራው ባሻገር፣ በዋነኝነት (በቀዳሚነት ብል ይሻላል0 የቦሌ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አገልጋይ እና የሰንበት ትምህርት ቤት መምህር መሆኑንም ጨምሬ ገለጽኩለት፡፡
ተማም በጣም ተገረመ፡፡ ‹‹አልሸባብ ሀብታሙን ቢያገኘው ኖሮ ይገድለው ነበር፡፡›› ሲል ከተናገረ በኋላም ለአምስት ደቂቃ ገደማ ያህል ከልቡ እንባው እየመጣ ጭምር ሳቀ፡፡ ተማምን ሳውቀው እንዲህ ለደቂቃዎች ያልተቋረጠ ሳቅ ሲስቅ ለመጀመሪዬ ስለነበረ በአግራሞት መመልከቴ አልቀረም፡፡ በእውነተኛ ሳቁ ውስጥ የተፈጠሩትን እንባዎች በጃኬቱ እስከመጥረግ ደረሰ፡፡ የተማም ሁለተኛ ልጅ የሆነው መሃመድ ከሳሎን ወጥቶ እኛ የተቀመጥንበት በረንዳ ድረስ መጥቶ ‹‹አባዬ ምንድን ነው እንዲህ ያሳቀህ? ንገረኝ?›› ሲል ጠየቀው፡፡ እነግርሃለሁ ብሎት ወደቤት ውስጥ ገባ፡፡
ከአግራሞቱ እና ከሳቁ መለስ ሲልም ‹‹ይሄ የክፍለ ዘመኑ ምርጥ ድራማ ነው››”

No comments:

Post a Comment

wanted officials