Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, July 22, 2015

(ሰበር ዜና) 6 የኦሮሞ ነፃነት ግንባሮች በቅንጅት አንድ ላይ ሊመጡ ነው * 4ቱ ተዋህደዋል

(ሰበር ዜና) 6 የኦሮሞ ነፃነት ግንባሮች በቅንጅት አንድ ላይ ሊመጡ ነው * 4ቱ ተዋህደዋል

Posted on  
OLF Army
(ዘ-ሐበሻ) አርበኞች ግንቦት 7 በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የሕወሓትን ሰራዊት የማጥቃቱ ዜና በተጧጧፈበት ወቅት የኦሮሞ ነፃነት ግንባርም በሐረር የሕወሓት የጦር ሰፈር ላይ በከፈተው ጥቃት 28 የሕወሓት ወታደሮችን መግደሉን ትናንት ድርጅቱ መግለጹን ዘ-ሐበሻ ማስነበቧ ይታወሳል:: ዛሬ በደረሰን ሰበር ዜና 6 የተለያዩ ኦሮሞ ነፃነት ግንባር ስም የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ወደ አንድ ላይ በመቀናጀት ለለውጥ መዘጋጀታቸውን ነው::
ለዘ-ሐበሻ የደረሰው ሰበር መረጃ እንደሚያመለክተው
1ኛ. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (በቦንሳ ሰባ የሚመራው)
2ኛ. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (በዶ/ር ኑሮ ደደፎ የሚመራው)
3ኛ. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጊዜያዊ አባሎች (በአቶ ድሪባ ወርዶፋ የሚመራው)
4ኛ. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ታጋዮች ቡድን (በአብደታ ሹኬ የሚመራው) ከጁን 27 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአንድ ላይ በመወሃድ በጋራ መስራት ጀምረዋል:: በቅርብ ቀናት ውስጥም የጀነራል ከማል ገልቹ እና በዳዑድ ኢብሳ የሚመሩት ኦነጎች ወደዚሁ ጥምረት እንደሚያመሩና በቅንጅት ትግሉን ለማጧጧፍ መዘጋጀታቸውን ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ተናግረዋል::
ጁን 27 2015 የተዋሃዱት አራቱ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር ስም የሚንቀሳቀሱት ድርጅቶች በአንድ አመራር ስር የሆኑ ሲሆን በጀነራል ከማል ገልቹም ሆነ በኦቦ ዳውድ ኢብሳ የሚመሩት ኦነጎች ይጠቃለላሉ ተብሎ ይጠበቃል::
ትግሉ እጅግ በጣም እየተቀጣጠለ በመጣበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ የተከፋፈሉና ትግሉን ወደ ኋላ የሚጎትቱ የኦነግ አመራር አባላት ላይ በውስጥም ሆነ በውጭ ከፍተኛ የሆነ ጫና እያጋጠማቸው መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ::
በ6ቱ በኦነግ ስም በሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች መካከል የሚደረገው ውህደትና ጥምረት በወቅቱ መራራ ትግል ላይ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ ያመጣል ተብሎ በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና በየጫካው የሚገኙ ብረት አንስተው በሚታገሉ ወገኖች ዘንድ ተስፋ ተጥሎበታል::
Source
1Ethiopia.wordpress.com

No comments:

Post a Comment

wanted officials