Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, July 28, 2015

የኢትዮያና የኬንያ ገዢዎች ሶማሊያን ለአራት ቦታ በመክፈል ለመቀራመት በሚስጥር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ዊክሊክስ ዘገበ

ሐምሌ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዊክሊክስ ባወጣው መረጃ ላይ የኢትዮያና የኬንያ ገዢዎች ሶማሊያን ለአራት ቦታ በመክፈል ለመቀራመት በሚስጥር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስነብቧል። ሶማሊያ ለም እና በማዕድን የበለጸገ ምድር ባለቤት በመሆንዋ የብዙ ሀገራትን ፍላጎትን ትስባለች።ዊክሊክስ ጅቡቲ ከሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ኤንባሲ መረጃውን እንዳገኘው ገልጿል።በአሁኑ ወቅት ብዙ አገራት በሶማሊያ ውስጥ ይገኛሉ፤የተወሰኑት በግፊት እንዲወጡ ተደርገዋል ብሎአል። ሶማሊያ ለአራት ክልል ትከፈላለች ሁለቱን ኢትዮጵያ ስትወስድ ቀሪውን ሁለቱ ደግሞ ወደ ኬንያ ይጠቃለላሉ። ሁለቱም አገራት 300 ሺህ ስኩዌር ካሬ ሜትር መሬትና ተጨማሪ አምስት ሚልዮን ሕዝብ ይደርሳቸዋል ይላል ዊክሊክስ በመረጃው። ኢትዮጵያና ኬንያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፈቃጅነት በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት በሽዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች በሶማሊያ አሰማርተዋል። ከዚህ በተጨማሪ ግን ሁለቱ አገራት በቀጠናው ድብቅ አጀንዳ እንዳላቸውና ኬንያ ወጣት ሶማሊያዊያንን በኪሲማዩ እያስታጠቀችና ስልጠናም እየሰጠች መሆኗንና ታጣቂዎችንም እንደምታግዝ ገልፆ ኢጣሊያም የኬንያንና የኢትዮጵያን ዓላማ እንደምትደግፈው ጨምሮ ገልፅዋል። ሶማሊያን ለመቀራመት መስማማታቸውን ዊክሊክስ መግለፁን በመቃወም ወይም በማስተባበል ሁለቱም አገራት ምንም ዓይነት ማስተባበያ አልሰጡም ሲል ዊክሊክስ ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials