Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, July 17, 2015

በወሊሶ ከተማ የገዢው መንግስት ወታደር ገበሬውን ለምን መሬቴን አላረስክም በሚል በጥይት አቆሰለው




የትህዴን ራድዮ እንደዘገበው በኦሮሚያ ክልል ወሊሶ ከተማና አካባቢው የሚኖሩ አርሶ አደሮች በኦሆዴድ ካድሬዎች “ለምን የኛ አገልጋዮች አትሆኑም?” እየተባሉ በላያቸው ላይ ግፍ እየተፈፀመባቸው እንደሚገኙ ተገለፀ።

ምንጮቻችን ከከተማዋ እንደገለፁት- በኦሮሚያ ክልል ወሊሶ ከተማ የሚገኙ አርሶ አደር ወገኖቻችን የካድሬዎች መሬት ተገደው እንዲያርሱት መደረጉን የገለጸው መረጃው አቶ ሲሳይ ከልካይ የተባለ የስርዓቱ የፖሊስ አባል ሰኔ 29/ 2007 ዓ/ም አቶ ጫላ ፈይሳ ለተባለ አርሶ አደር “መሬቴን ለምን አላረስክልኝም” በማለት ስለ አፋጠጠበት አርሶ አደሩም “በኔ ጉልበት ልትጠቀም; ልታስፈራራኝ አይገባህም” ስላለው ብቻ ፖሊሱ ጥይት ተኩሶ እጁን ስለአቆሰለው አቶ ጫላ ፈይሳ በከባድ ቆስሎ ወሊሶ ሆስፒታል ተኝቶ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው ይህ የስርአቱ ካድሬዎች የግፍ ተግባር በወሊሶ ከተማ ብቻ የታየ ሳይሆን በሁሉም የሃገራችን አካባቢዎች እየታየ ያለና የነበረ መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል፤ ምእራብ ሸዋ ዞንና አካባቢው የሚኖሩ አርሶ አደሮች ማዳበርያ በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት አልቻልንም ብለው ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በማሰባቸው እየታሰሩ እንደሆኑ ተገለፀ።

በመረጃው መሰረት በኦሮሚያ ክልል፤ ምእራብ ሸዋ ዞን፤ ኖኖ ወረዳና አካባቢው የሚኖሩ አርሶ-አደሮች በያዝነው ዓመት ውስጥ መንግስትን ሁሉንም አርሶ-አደር በሚጠቀምበት መንገድ በተመጣጣኝ ዋጋ ማዳበርያ ልያቀርብልን አልቻለም በማለት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በመጠየቃቸው ብቻ 15 የሚያህሉ አርሶ-አደሮች አነሳሾች ተብለው መታሰራቸውን ታወቀ።

ህጋዊ በሆነ መንገድ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቂያቸውን ስላቀረቡ ብቻ በስርዓቱ እንደ ጠለት ታይተው ከታሰሩት አርሶ-አደሮች መካከልም ክብረቴ ዳርጌ፤ ደብለው ቢተው፤ ፍቃዴ ደሳለኝና ሌሎችም እንደሚገኙባቸው መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45107#sthash.egEaPNdL.dpuf

No comments:

Post a Comment

wanted officials