የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አቤቱታ ነገ ውሳኔ ያገኛል
ነገ ሐምሌ 22/2007ዓም ከሰዓት 8:00 ሰዓት 6 ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሰበር ሰሚ አቤቱታ ውሳኔ ይገኛል።
ከታሪኩ ደሳለኝ
ተመሰገን አንዱን ጋዜጣ ሲዘጉበት በሌላ መንገድ እየመጣ አዱን በር ሲዘጉ ሌላ እየሰበረ ዱላና እንግልታቸውም ማባበያና ማስፈራሪያቸውን ንቁ ወደ ፍርሀት ፊቱን ሳያዞር ለሀገሬ ስል እሰከ ቀራኔዮ ነዉ ጉዞዬ እንደለ አለ። ገና ከሱ የተጀመረ ዕለት ተመስገን ለፍርድ ቤቱ ይህን መናገሩ ይታወቃል። እዚህ ፍርድ ቤት ሰቆም በሀገሬ ሰማይ ስር ፍትህ እንደሌለ አጥቼው አይደለም፣ ነፃ እወጣለሁ ብይ አሰቢም አልመጣሁም፣ ወሳኔው የናተ ደኞች እንዳልሆነ የፖለቲካ ውሳኔ እንደሆነና ከክሱ በፊት እንደተፈረደብኝም አውቃለሁ ታውቃላችሁ፣ አዚህ የተከሳሽ ሳጥን ውስጥ ስቆም ፍርዱ የህዝብና የታሪክ ነው ብዬ ነው። የተከሰስኩባቸው ፁሁፎቼ የማምንባቸው ሀሳቦቼ ናቸው። ወድጄ ፈቅጄ የፃፍኳቸው ናቸው፣ ዛሬም ነገም ደግሚ የምፅፋቸው ናቸው። ለሀገሬ ይበጃታ ብዬ የማምነውን ነገር ሁሉ ከማድረግ ከእምነቴ ላንድ አፍታ እንኳን ወደ ኃላ እንደማልል እንድታውቁ እፈልጋለሁ። የምታደርጉት ነገር ሁሉ አያስቆመኝም፣ መሆን ያለብኝን ሁሉ ለሀገሬ ስል እሆናለው፣ጉዞዬ እስከ ቀራኒዮ ድረስ ነው። ማለቱን እናስታውሳልን ያስታውሳሉ። ተመስገን የተናገርከውን በመሆን ግንባርህንም ቃልህንም ባለማጠፍህ በበርሃ ውስጥ አስረውህ ትገኛለህ። ለገጠመህ የጀርባና የጆሮ ህመም ህክምና እንዳታገኝ አድርገውሀል። ያለ ፍርሀት የመንከውን በመፅፍህ ወንጀል ብለው ያእሰሩበትን ሂደት እንኳን እንዳትከታተል አደርገውሀል። ቢሆንም ግን በእምነትህ ፀንተህ በዙዎችን አፍርተህ ሀሳብ እንደማይታሰር አሳይተህነሀል አሳይተሀቸዋል። ለሀገሬ ስል ነው ያልካት ሀገርህም አረሳችህም አትረስክምም።
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45394#sthash.QAbasAhu.dpuf
No comments:
Post a Comment