የአስቴር ቤተሰቦች ደብዳቤ:- ‹‹የእናት ጡት እየፈለገ በሚያለቅሰው ህጻን እማጸናችኋለሁ››
by Dawit Solomon
ከጎንደር ተነስታ ስራ ፍለጋና ፓስፖርቷን ለማደስ ወደ አዲስ አበባ እንዳመራች በፌደራል ፖሊስ አባላት ተይዛ ማዕከላዊ ስቃይ ቤት መግባቷን የሚናገሩት የአስቴር(ቀለብ)ስዩም ቤተሰቦች ፍርድ ቤት ቀርባ በሽብርተኝነት መከሰሷን መስማታቸውን ይናገራሉ፡፡ በመንግስት መስሪያ ቤት ትሰራ የነበረችው አስቴር በምትኖርበት አካባቢም የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ውስጥ ትሰራ በነበረበት ወቅት ከሃላፊዎቿ የተለያዩ ጥያቄዎች ሲቀርቡላት ቆይተው በመጨረሻም ለጥያቄያቸው ፈቃደኛ ሳትሆን በመቅረቷ ከስራ እንዳባረሯት ይገልጻሉ፡፡ በሞያዋ በአገሯ መስራት የተነፈገችው አስቴር በቤተሰቦቿ አገለለጽ በንዴትና በስሜት ተገፋፍታ አንድነት ፓርቲን ተቀላቀለች፡፡የስምንት ወር ልጅና በእድሜ የደረጁ እመዋ ያሏት በቤት ስሟ ቀለብ ወደ አዲስ አበባ ለስራ ፍለጋ እንዳመራች በቁጥጥር ስር እንድትውል ተደረገች፡፡ በደብዳቤው የተሳተፉት ወላጅ እናቷ እናቱን በግፍ የተነጠቀችውን ህጻን ልጃቸውን በስተርጅና ታቅፈው መቅረታቸው ሊሸከሙት የማይችሉት ሆኖባቸው ‹‹መንግስት እንዲፈታልኝ››ብለዋል፡፡የሚማጸኑት ደግሞ ‹‹የእናት ጡት እየፈለገ›› በሚያለቅሰው ህጻኑ ስም ነው፡፡ይሰሟቸው ይሆን ? ይህ በእዲህ እያለ የአስር ወር ልጇ ጋር ነጥላችሁ መጫት ልጃችን ቀለብን ምንም በለለችበት አሸባሪ የሚል ስም ሰጥቶ ማሰሩ ተገቢ አለመሆኑንና ሃላፊነቱን እኛ ልንወስድ በኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሁም የእናት ጡት እያለ በሚያለቅሰው ልጅ ስም እንድትፈቱልን በአክብሮት እንጠይቃለን። እንለምናለን።
No comments:
Post a Comment