Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, July 30, 2015

ከእስር የተለቀቁ ጋዜጠኞችና ጦማርያን የጋዜጠኝነት ስራ ለመስራት እንደሚፈሩ ገለጹ

ከእስር የተለቀቁ ጋዜጠኞችና ጦማርያን የጋዜጠኝነት ስራ ለመስራት እንደሚፈሩ ገለጹ
ኢሳት ዜና (ሃምሌ 22, 2007)
በቅርቡ ክሳቸው ተቋርጦ በነጻ የተሰናበቱት ጋዜጠኞች ወደ ቀድሞ ሞያቸው ለመመለስ ፍራቻ አድሮባቸው እንደሚገኝ ገለጡ።
ከአንድ አመት በላይ ከስድስት ጦማሪያን ጋር በሽብርተኛ ወንጀል ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት ጋዜጠኛ ዘላለም ክብረት እና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ ወደ ጋዜጠኝነት ላመመለስ ፍራቻ አድሮባቸው እንደሚገኝ ከCBS ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ መልልስ ገልጸዋል።
ይሁንና የእስር ጊዜዋን አጠናቅቃ በቅርቡ የተፈታችው ጋዜጠኛ ሙያዋን እንደምትቀጥልና መስዋእትነትም ለመክፈል መዘጋጀቷን አስታውቃለች ።
የፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ጉብኝትን አስከትሎ ከጋዜጠኞቹ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረገው የቴሌቪዥን ጣቢያው ጋዜጠኛ ሪዮት ሙያው የሚጠይቀውን ዋጋ ለመክፈል ራሱዋን እንዳዘጋጀች ገልጿል።
“ስለዚህ መንግስት አለመጻፍ፣ አልያም ሙያዬን ተግባራዊ አድርጌ መስዋትነት ለመክፈል ያሉኝ ሁለት አማራጮቼ ናቸው” ያለችው ጋዜጠኛዋ ስራዋን ቀጥላ የሚመጣባትን ለመቀበል መወሰኗን አስረድታለች።
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ከጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ጋር ባደረጉት የግል ውይይት ጋዜጠኞችን ማሰር የሰባዊ መብት ጥሰት ብቻ ሳይሆን አቶ ሀይለማሪያም የሚሹትን የውጪ ኢንቨስትመንት ጉዳይ እንደሆነ ኦባማ መናገራቸውን የቴሌቪዥን ጣቢያው ዘግቧል ።
ኢትዮጵያ መለወጥ ይኖርባታል፣ እኔም የሆነ አስተዋጾ ማድረግ ይኖርብኛል ስትል ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በቃለ ምልልሷ ገልጻለች።


No comments:

Post a Comment

wanted officials