የኢትዮጵያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከአደጋ ተረፈ
ባሳለፍነው ሐሙስ ከቀኑ 11፡30 ከቡጁምቡራ ተነስቶ ናይሮቢ በማረፍ የአዲስ አበባ መንገደኞችን መጫን ይገባው የነበረው ንብረትነቱ የኢትዮጵያ የሆነ የመንገደኞች አውሮፕላን ከተያዘለት የጊዜ ገደብ አርፍዶ ቢደርስም ናይሮቢ ከደረሰም በኋላ ለተጨማሪ 45 ደቂቃዎች እንዲዘገይ ተደርጓል ፡፡
አውሮፕላኑ የአንድ ሰዓት ከአርባ ደቂቃ በረራውን ለማድረግ ከናይሮቢ ከተነሳና የአንድ ሰዓት በረራ ካደረገ በኋላ ተሳፋሪዎቹን የሞት ፍርሃት ውስጥ የከተተ ሁኔታ አጋጥሞታል፡፡አውሮፕላኑ ከተፈቀደለት የከፍታ ጫማ በላይ በመውጣቱ ተሳፋሪዎቹ የመተንፈስ ችግር አጋጥሟቸው አረቴፊሻል ኦክሲጂን ለመውሰድ ተገድደዋል፡፡
አውሮፕላኑ ወደ አዲስ አበባ ሊያደርግ የነበረውን በረራ በማቋረጥም በድጋሚ ወደ ናይሮቢ አንዲመለስ ተደርጓል፡፡ናይሮቢ ጆሞ ኬንየታ ኤርፖርት ከማረፉ በፊትም ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ነዳጁን ለመጨረስ አካባቢውን መዞሩ ታውቋል፡፡አውሮፕላኑ በሰላም ካረፈ በኋላም በውስጡ ተሳፍረው የነበሩ መንገደኞች በሌላ አውሮፕላን እንዲበሩ ተደርገዋል፡፡
ከመነሻው አውሮፕላኑ ችግሮች እንደነበሩበት እየታወቀ 180 ተሳፋሪዎችንና የአውሮፕላኑን ሰራተኞች ይዞ እንዲበር መደረጉ ግን ምላሽ የሚያሻው ጥያቄ ሆኗል፡፡የዜናው ምንጮች የአውሮፕላኑ ተሳፋሪዎች ናቸው፡፡

No comments:
Post a Comment