Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, July 7, 2015

መንግስት በሕዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ላይ ‹‹ጥፋተኝነት›› ወሰነ!

ሰበር ዜና!
መንግስት በሕዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ላይ ‹‹ጥፋተኝነት›› ወሰነ!
የቅጣት ውሳኔ ለሐምሌ 27/2007 ተቀጥሯል!!!
ፍርዱን አስመልክቶ የ‹‹ድምጻችን ይሰማ!›› ገጽ መግለጫ ከቆይታ በኋላ የሚቀርብ ይሆናል!
ሰኞ ሰኔ 29/2007
ንጹሃን የህዝብ ወኪሎችን ያለአንዳች ጥፋት ለ35 ወራት በእስር ሲያንገላታ የቆየው የኢትዮጵያ መንግስት የ‹‹ጥፋተኝነት›› ፍርድ በሁሉም ታሳሪዎቻችን ላይ ፈረደ!
በመጨረሻ ሰዓት ከደህንነቶች ትእዛዝ የሚቀበሉ ዳኞችን ችሎቱ ላይ በመመደብ የጥፋተኝነት ፍርድ ያስተላለፈው መንግስት 18 ታሳሪዎቻችን ላይ የጥፋተኝነት ብይን በማስተላለፍ በሃይማኖት ጣልቃ አለመግባቱን እና በቀበሌ የተካሄደው የመጅሊስ ምርጫም እንከን አልባ መሆኑን ገልጿል፡፡ በመሆኑም በተከሰሱበት የጸረ ሽብር አንቀጽ ‹‹የመቀስቀስ፣ የማነሳሳት እና የማሴር›› ወንጀል ሁሉንም ታሳሪዎች በፈጻሚነት እና በተባባሪነት ጥፋተኛ ብሎ ፖለቲካዊ ውሳኔ ወስኖባቸዋል፡፡ የቅጣት ፍርድ የፊታችን ሐምሌ 27/2007 እንደሚሰጥ በመግለጽም የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃ አስተያየት ከዚያ በፊት እንዲቀርብ ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡
ይህ እጅግ አሳዛኝ እና አሳፋሪ ፍርድ ኮሚቴዎቹን እና አጋሮቻቸውን በወከላቸው መላው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ላይ የተበየነ የጥፋተኝነት ፍርድ ሲሆን ብይኑን አስመልክቶም ሰላማዊ ትግላችን ያለው አቋም ከቆይታ በኋላ በይፋ መግለጫ የሚቀርብ ይሆናል።
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

No comments:

Post a Comment

wanted officials