ህወሃት የሚመራዉ የመከላከያ ሰራዊት የዘመቻ መምሪያና ክትትል ቢሮ እንዲሁም የመከላከያ ደህንነት የበላይ ሃላፊዎች
በአርበኞች ግንቦት 7 የከፈተበትን ጦርነት ለመከላከያ ሚኒስቴር በማመልከት በአስቸኳይ የመከላከያ ሐይል ተጨምሮ
ስፍራዉን የመልሶ ማጥቃት የጦር ክልል ካላደረግነዉ በስተቀር የተዋጊዎቻችዉ የጦር ስልት ከባድና የሚያሰጋ መሆኑን ገልጿል።
በመሆኑም የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት የከፈተዉን ጦርነት መልሶ ያጠቃል የተባለ ሐይል ከጎንደርና ከወሎ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በሰሞኑ በተደረገ ጦርነት ብቻ የ 44 ተኛ እና የ24 ተኛ ክ/ጦሮች መፍረክረካቸዉ እራስ ምታት የሆነበት ወታደራዊ ደህንነት የተባለዉ የወያኔ ክንፍ ሻቢያ ጦርነት ከፈተችብን በሚል መንፈስ መረጃዉ ለህዝብ እንዲገለጽና ኢቢሲ የቀድሞዉ ኢቲቪ በተባለዉ የቴሌቪቭን ጣቢያ
የተቀናበረ የሃሰት ዶክመንተሪና ዜና እንዲሰራ ትእዛዝ እንዲተላለፍ ጠይቋል።
በተያያዘ ዜና አርበኞች ግንቦት 7 በሁመራና በወልቃይት ጠገዴ እንዲሁም በአርጃሞ አካባቢ ሶስት ስፍርዋዎች ሲያጠቃ
በተጨማሪ በኦጋዴን (የኦጋዴን ነጻ አዉጭ ) በኬንያ በተለይም ሞያሌ አካባቢ ኦነግ (የኦሮሞ ነጻነት ግንባር )
በተጨማሪ በቡሬና በካባቢዉ ትግራይ ትህዴን ( የትግራይህ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ) በአፋር የአፋር ህዝብ ነጻነት
ግንባር ጉሬላ በተባለዉ የዉጊያ ስልት ጦርነት መተንኮሳቸዉ ጉዳዩ ጥምርና ጀርባዉ የከበደ ነዉ ሲል ወታደርራዊ ደህንነቱ
ፍራቻዉን ገልጿል።