Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, July 9, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት-ከአፋር ነፃ አውጭዎቹ ኦብነግ አርዱፍና ጋዲሌ ጋር በመቀናጀት

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት
በህወሓቶች ቤት ውስጥ ታላቅ ሽብር ነግሷል ከወልቃይቱ /ቃፍታ መሲን፣ ኮርጃሙስ፣ ማይ ሰገን፣ በዋል፣ ንኳል ሳግላ እና ማይ እምቧ…/ የአርበኞች ግንቦት 7 ወታደራዊ እርምጃ በኋላ ማለስልጣናቱ እንደተነፈሰ ፊኛ በመልፈስፈስ ኩምትርትር ጭምትርትር ብለዋል፡፡
የጦርነት ደመና ካጠላበት የኢትዮጵያ ጠቁር ሰማይ ስር በፍርሃት ተሸብበው የሚገኙት የህወሃት ባለስልጣናት እና ጀነራሎች የጨነቃቸውን ያክል ሰራዊቱን ወዲያ ወዲህ በማተራመስና በማንጓለል በድሃ ልጅ ዥዋዥዌ በመጫዎት ላይ ናቸው፡፡ ኤታማጆር ሹሙ "ጀነራል" ሳሞራ የኑስ ሰራዊቱ ኋላቀር እንደሆነ ህወሓቶች ባደረጉት ምስጢራዊ ስብሰባ ላይ አምኗል፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ ከመጀመሩ ከወራት በፊት ግን አገሪቱ በወታደራዊ አቅሟ ከዓለም አገሮች ጋር ተወዳድራ ከዓለም በ46ኛ ከአፍሪካ ደግሞ በ4ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ብለው ያን የተለመደ የፕሮፖካንዳ ቱልቱላቸውን ነፍተው ነበር፡፡
አሁን ኋላቀር በማለት ያጣጣሉትን ለእርድ የተዘጋጀ ሰራዊት በአራቱም የአገሪቱ ማዕዘናት እየበተኑት ይገኛሉ፡፡ የሰሞኑ ወደ ሰሜን የሚደረገው እንቅስቃሴ እንዳለ ሆኖ ትናንት ጠዋት ከአዋሳ በሀገረ ማርያም በኩል ወደ ሞያሌ እና ሌሎች ጠረፎች አካባቢ በርካታ ሜካናይዝድና እና እግረኛ ጦር እንዲሁም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ፌደራል ፖሊስ ተጭኖ ተልኳል፡፡
የሀገረ ማርያም ዓይን እማኞች 26 አሮጌ ታንኮች በሚንገራገጭ ድምፃቸው አካባቢውን በማወክ እንደ ኤሊ እያዘገሙ ሲያልፉ መቁጠራቸውን ለዜና ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ ወደ ዚህ አካባቢ ጦር በገፍ እየተጫነ የሚገኘው የኦነግ ጎሬላ ተዋጊዎች ጥቃት ለመክፈት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ የሚያረጋግጥ መረጃ ስለደረሳቸው መሆኑ ታውቋል፡፡
ከአፋር ነፃ አውጭዎቹ አርዱፍና ጋዲሌ ጋር በመቀናጀት ኦብነግ በአፋር ክልል ሰርጎ እንደገባ የሚያመላክት መረጃም ጭምር ስለደረሳቸው ወደ አፋር ክልልም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጦር እያጓጓዙ ይገኛሉ፡፡
ከዚህ መተራመስና መታመስ ጋር ተያይዞ ጦር እየመሩ በየማዕዘናቱ በሚላኩት ወታደራዊ አዛዦችና የበላይ አለቆቻቸው መካከል የተካረረ ፀብ እየተፈጠረ መሆኑን ከመከላከያ ምንጮቻችን የደረሰን መረጃ ያረጋግጣል፡፡ የፀቡ መንስኤ እያንዳንዱ አዝማች "የተመደበልኝ የሰው ሃይል እንዲሁም ትጥቅና ስንቅ ያንሰኛል..." የሚል ሰበብ ማንሳቱ መሆኑ ታውቋል፡፡ ይህም የሚያመላክተው የህወሓት ወታደራዊ አዛዦች ወኔያቸውን መሽናታቸውን ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የህወሓት ዘረኛ ቡድን ሰራዊት ከማተራመሱ ጎን ለጎን ህዝብ በገፍ እያፈነ ወዳልታወቀ ቦታ ይዞ መሰወሩን በርትቶበታል፡፡ በተለይም አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር ጎንደር... በርካታ ሰዎች በታጠቁ ኃይሎች እየታፈኑ ወዳልታወቀ ቦታ በመወሰድ ላይ ናቸው፡፡
የሰሜን ጎንደር ዞን የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ የነበረውና ጎንደር መምህራን ኮሌጅ ውስጥ የሚያስተምረው መምህር አለላቸው አታለለ ትናንት ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ የህወሓት የታጠቁ ቡድኖች ወደ መኖሪያ ቤቱ ገብተው አፍነው ወስደውታል፡፡ መምህሩ እስካሁን ድረስ የት እንዳለ አይታወቅም፡፡
በተጨማሪም የጎንደር እና አካባቢውን ገበሬዎች የህወሓት ካድሬዎች ዋጋውን መቶ በመቶ ቅድሚያ ካልከፈላችሁ በማለት ማዳበሪያ እንዳይወስዱ ከልክለዋቸዋል፡፡ ገበሬው የባሰውኑ በህወሃት ልቡ ሻክሯል...

No comments:

Post a Comment

wanted officials