ሁለት የአላባማ ካውንቲ ፍርድ ቤቶች ውሳኔውን ውድቅ በማድረግ ምንም አይነት የተመሳሳይ ጋብቻ የምስክር ወረቀት የማይሰጡ መሆናቸውን ገልጸው ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ዳግም እንዲያጤነው ጠይቀዋል። ከዚህም በተጨማሪ የቴክሳስ ከፍተኛ አተርኒ ተመሳሳይ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በግለሰብ ነጻነት ስም ሰዎች ሰብአዊ ክብራቸውን እንዲያዋርዱ መፍቀድ የለብንም የሚሉ አሜሪካውያን በየግዛቱ ተቃውሞ በማሰማት ላይ ናቸው።
አንድ ታዋቂ የቤተክርስትያን ፓስተር በበኩላቸው በሚያገለግሉበት ቤተክርስትያን እንጋባ ብለው የሚመጡ ተመሳሳይ ጾታዎችን የማያስተናግዱ እንደሆነ ተናግረው በዚህ ምክኒያት ህገ መንግስቱን ጥሰሀል ተብዬ ብከሰስ ማንኛውንም ቅጣት ለመቀበል ዝግጁ ነኝ በማለት በይፋ ተናግረዋል። እኚሁ ፓስተር እግዚአብሄር በአንድ ወቅት እስራኤላውያንን በዚሁ ድርጊታቸው እንደቀጣቸው ሁሉ አሜሪካንንም ደግሞ ያጠፋታል በማለት መንግስትን አስጠንቅቀዋል።
የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በአምላክ ፊት አስጸያፊና አሳፋሪ መሆኑ በቅዱስ መጽሀፍ የተገለጸ እንዲሁም ለሰብአዊ ህይወት መቀጠል አደገኛና ኢሞራላዊ ድርጊት መሆኑን ሶሾሎጂስቶች ደጋግመው ይናገራሉ።
(የትነበርክ ታደለ)