በህወሓት መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ተፈጥሮ የቆየው መከፋፈል በሁለት ፅንፍ የቆመ ሲሆን አንደኛው ቡድን በኤታማጆር ሹሙ ጀነራል ሳሞራ የኑስ ስር ሁለተኛው ቡድን ደግሞ የምስራቅ ዕዝ አዛዥ ከነበረው ሌ/ጀነራል አብርሃ ወ/ማርያም ጎን የተሰለፉ ናቸው፡፡ ሌ/ጀነራል አብርሃ ወ/ማርምን ከዕዝ አዛዥነቱ አንስቶ ወደ መከላከያ መምሪያ የማዛወሩ የእነ ጀነራል ሳሞራ የኑስ ቡድን ዕቅድ በሌ/ጀነራል አብርሃ ቡድን የበላይነት ሊከሽፍ ችሏል፡፡ ሆኖም ግን ሌ/ጀነራል አብርሃ ወ/ማርያም ከምስራቅ ዕዝ ተነስቶ የደቡብ መስራቅ ዕዝ አዛዥ መሆኑ ታውቋል፡፡
ሳሞራና ተከታዮቹን በተፃረረ መልኩ ከሌ/ጀነራል አብርሃ ወ/ማርያም ጎን ከተሰለፉት የህወሓት ጀነራሎች መካከል የመከላከያ ስልጠና መምሪያ ዋና አዛዥ ሌ/ጀነራል ሰአረ መኮንን፣ የአግአዚ ኮማንዶና ልዩ ኃይሎች ጠ/መምሪያ ዋና አዛዥ ብ/ጀነራል ገ/መድህን ፈቃዱ እና የተዋጊ መሃንዲስ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ብ/ጀነራል ሙሉ ግርማይ ይገኙበታል፡፡
ሌ/ጀነራል አብርሃ ወ/ማርያም ቀደም ሲል ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ኃላፊው ጌታቸው አሰፋ ጋር በነበረው የቆየ ግጭት የደህንነቱ ቁንጮ ጌታቸው አሰፋ ከሳሞራ የኑስ ጎን ሊሰለፍ ችሏል፡፡
በተጨማሪም ሁለቱም ጎራ ለይተው እርስ በርሳቸው የተሰላለፉት ቡድኖች የኢንሳ /የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ/ ዋና ኃላፊ የሆነውን ሜ/ጀነራል ተ/ብርሃን ካህሳዬን በየጎናቸው ለማሰለፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ አደገኛ ፉክክር ውስጥ የገቡ ሲሆን ሜ/ጀነራል ተ/ብርሃን እስካሁን ድረስ የትኛውን ቡድን እንደሚደግፍ በግልፅ አቋሙን ባያሳውቅም በሌ/ጀነራል አብርሃ ወ/ማርያም ስር ለተሰባሰቡት የህወሓት ጀነራሎችና ሌሎች መኮንኖች በጎ አመለካከት እንዳለው ኢንሳ ውስጥ የሚሰሩ የጀነራሉ የልብ ወዳጆች ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀ