ከጎንደር ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው አይምባ በተባለ አካባቢ ትናንት በደረሰ የተሸከርካሪ አደጋ 10 ሰዎች ሞተዋል::
አደጋው የደረሰው ልዩ ስሙ አዘዞ ሎዛ ማርያም አይነኩራ በተባለ አካባቢ፥ ከተቃራኒ አቅጣጫ ይጓዙ የነበሩ ሁለት ሚኒባሶች እርስ በእርስ በመጋጨታቸው ነው፡፡
ትናንት 7 ሰዓት ከ30 ላይ በደረሰው የትራፊክ አደጋ 10 ሰዎች ሲሞቱ በ22 ተሳፋሪዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል፡፡
አደጋው የደረሰው ልዩ ስሙ አዘዞ ሎዛ ማርያም አይነኩራ በተባለ አካባቢ፥ ከተቃራኒ አቅጣጫ ይጓዙ የነበሩ ሁለት ሚኒባሶች እርስ በእርስ በመጋጨታቸው ነው፡፡
ትናንት 7 ሰዓት ከ30 ላይ በደረሰው የትራፊክ አደጋ 10 ሰዎች ሲሞቱ በ22 ተሳፋሪዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል፡፡
በአደጋው የሁለቱም ተሽከርካሪዎች ሾፌሮች ህይዎት አልፉአል::
ጉዳት የደረሰባቸው መንገደኞችም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።
የአደጋው መንስኤ ሁለቱ ተሽከርካሪዎቹ እርስ በእርስ ቦታ በመዘጋጋት የፈጠሩት የፊት ለፊት ግጭት መሆኑም ታውቛል::
ከአይምባ ወደ ጎንደር ይጓዝ የነበረው ኮድ 3 ሚኒባስ ትርፍ አሳፍሮ እንደነበር ጠቅሰው፥ ከጎንደር አይምባ ይጓዝ የነበረው ኮድ 2 ሚኒባስ ደግሞ አምስት ተሳፋሪዎች በውስጡ ነበሩ፡፡
No comments:
Post a Comment