Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, March 18, 2016

በኬንያ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያንና ናይጀሪያውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ



የኬንያ ፖሊስ ወደ ሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል ያላቸውን ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያንና ናይጀሪያውያን በቁጥጥር ስር አዋለ።
የሃገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች ከቀናት በፊት 23 ኢትዮጵያውያንን በተመሳሳይ ሁኔታ ከያዙ በኋላ 114 ስደተኞች በቁጥጥር ስር ሲዉሉ የመጀመሪያው መሆኑን ዘስታንድራድ የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል።
114 የሚሆኑት የኢትዮጵያን የናይጀሪያ ስደተኞች በመዲናይቱ ናይሮቢ ኑአሪካ ተብሎ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የተያዙ ሲሆን፣ ምን ያህሉ ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ የታወቀ ነገር የለም።
የፖሊስ ኮሚሽነት የሆኑት አሊስ ኪሚሌ ስደተኞቹን በቁጥጥር ስር ከማዋሉ በፊት ክትትል ሲካሄድ መቆየቱን አስታውሰው ሁሉም ስደተኞች ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።
የኬንያ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት በየዕለቱ ወደሃገሪቱ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ መንገስት ተጨማሪ በጀትን በመመደብ በድንበር አካባቢ ከፍተኛ ጥበቃ እንዲደረግ ጥያቄን ማቅረባቸው መዘገባቸን ይታወሳል።
ወደሃገሪቱ በመሰደድ ላይ ያሉት ኢትዮጵያውያን ወደ ደቡብ አፍሪካ የመጓዝ እቅድ እንዳላቸውም ስደተኞቹን የኬንያ ፖሊስ አስታውቋል።
የኬንያ ኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ የድንበር አካባቢ ከ20 የሚበልጡ የቁጥጥር ጣቢያዎች ቢያቋቁሙም የኢትዮጵያውያኑ ስደት ከመቀነስ ይልቅ እየጨመረ መምጣቱንም ጋዜጣው ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ በዘገባው አስነብቧል።
የአለም አቀፍ ስደተኛች ድርጅት (አይኦኤም) በየዕለቱ በትንሹ ወደ30 ኢትዮጵያውያን ወደጎረቤት ኬንያ በመሰደድ ላይ መሆናቸውን በቅርቡ ማስታወቁ ይታወሳል።
በአሁኑ ወቅትም ኬንያን ጨምሮ በታንዛኒያ፣ ናሚቢያ፣ ዚምባቡዌና በሌሎች የምዕራብ አፍሪካ ሃገራት በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኖች በእስር ቤት እንደሚገኙም ለመረዳት ተችሏል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials