Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, March 1, 2016

ቤተ-እስራዔላውያንን ለማጓጓዝ የወጣው እቅድ እንዲዘገይ ተደረገ

ቤተ-እስራዔላውያንን ለማጓጓዝ የወጣው እቅድ እንዲዘገይ ተደረገ

ቤተ-እስራዔላውያንን ለማጓጓዝ የወጣው እቅድ እንዲዘገይ ተደረገ

ኢሳት (የካቲት 18 ፥2008)
Israel Assoc. for Ethiopian Jews
በቅርቡ የመጨረሻዎቹ ዘጠኝ ሺህ ቤተ-እስራዔላውያን ከኢትዮጵያ ወደእስራዔል ለማጓጓዝ ቃል ገብታ የነበረችው እስራዔል እቅዱ እንዲዘገይ ማድረጓን አርብ ይፋ አደረገች።
የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ እቅዱ ከበጀት ጋር በተያያዘ እንደዘገይ መደረጉን ቢገልፅም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አካላት ድርጊቱ በእስራዔል ጥያቄን አስነስቶ ካለው ከዘረኝነት ጉዳይ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ገልጸዋል።
የእስራዔል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ጄኔራል ዳይሬክተር የሆኑት ኤሊ-ግሮነር እቅዱ ከመነሻውም በጀት ሳይያዝለት መፅደቁን ይፋ ማድረጋቸውን ሃርቴዝ የተሰኘ የሃገሪቱ ጋዜጣ አርብ ዘግቧል።
ወደ ዘጠኝ ሺ የሚጠጉ ቤተ-እስራዔላዊያን ከአዲስ አበባ ወደ እስራዔል ለማጓጓዝ 750 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የገለጹት ሃላፊው የሃገሪቱ በጀት ዳግም ውይይት እስከሚካሄድበት ድረስ እቅዱ እንደሚዘገይ አስታውቀዋል።
የእስራዔል መንግስት ለአመታት በጎንደርና በአዲስ አበባ ጉዞን ሲጠባበቁ የነበሩት ቤተ-እስራዔላውያን በ120 ቀናት ውስጥ ኣንደሚያጓጉዝ ይፋ አድርጎ እንደነበር ይታወሳል።
ከሶስት ወር በፊት ፀድቆ የነበረው ይኸው ውሳኔ ሁሉንም ተጓዦች በአምስት አመት ውስጥ ለማጓጓዝ እቅድን ነድፎ እንደነበር ጋዜጣው አስነብቧል።
መንግስት እቅዱ ከባጀት ጋር በተያያዘ እንደሚዘገይ መግለጹን ተከትሎም በርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ድርጊቱ በሃገሪቱ ተንሰራፍቶ ካለው የዘረኝነት ድርጊት ጋር በተያያዘ ነው በማለት ተቃውሞን አቅርበዋል።
ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘት አመታትን ሲጠብቁ የነበሩ በሁለቱም ሃገራት ያሉ ቤተ-እስራዔላውያንም፣ የመንግስት እርምጃ ተገቢ አለመሆኑን በመግለፅ ቅሬታቸውን እያቀረቡ እንደሚገኝ ታውቋል።
በእስራዔል በውትድርና ሙያ ላይ የተሰማራችውና አያቷንና ሶስት የአክስት ልጆቿን በመጠባበቅ ላይ የነበረችውን ቸን አስማማው እቅዱ በበጀት ምክንያት እንደገዘይ ተደርጓል የሚለውን ውሳኔ እንደማያሳምናት ለሃርቴዝ ጋዜጣ አስረድታለች።
በውትድርና ሙያ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ በርካታ ቤተ-እስራዔላውያን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘት ጉጉት እንደነበራቸውና እርምጃው ከፍተኛ ተቃውሞ መቀስቀሱንም የእስራዔል መገናኛ ብዙሃን አርብ አስነብበዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials