Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, March 31, 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት ---·አበራ ጎባው ለሌሎች የኢትዮጵያ ጭቁን ገበሬዎች ትልቅ የትግል መምህር

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት
·አበራ ጎባው ለሌሎች የኢትዮጵያ ጭቁን ገበሬዎች ትልቅ የትግል መምህር እና የምንጊዜም አይበገሬ ጀግና የነፃነት ፋኖ…
=====================
12439482_205198099855414_6925038051583172580_nየህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ዘረኛ ቡድን ጭቆና ግፍና በደል ሁሉንም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ያዳረሰ ከዓመት ዓመት በእጅጉ እየከፋና እየበረታ የመጣ ነው፡፡ ነገር ግን በተለየ ሁኔታ መራራ የሆነ የበቀል እርምጃ እየወሰደባቸው የሚገኙ የተለዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ የወህሓት የበቀል በትር እየገረፋቸው ከሚገኙ የኢትዮጵያ ክፍሎች ደግሞ ጎንደር አርማጭሆ አንዱ እና በግንባርቀደም የሚጠቀስ ነው፡፡
የህወሓት ታጣቂዎች የአርማጭሆን “እምቢ አልገዛም!” ያለውን ብቻ ሳይሆን ሰላማዊዩን ወጣት ጭምርም በጥይት እየጨፈጨፉ አስከሬኑን ለመቀጣጫ ገብያ ላይ በተደጋጋሚ አስጥተውታል፤ በመኪናም ጎትተውታል፡፡ ቀይ ሽብርን በጥቁር ሽብር ቀይረው በርካታ ህዝብ እያፈሱ ወደ ሁመራ በመውሰድ በቅድሚያ መቀበሪያውን እያስቆፈሩ ረሽነውታል፡፡ የቀረውን ደግሞ እያፈኑ ወደ አዲስ አበባ በማጋዝ ማዕከላዊ አጉረው ጥፍሩን በፒንሳ እየነቀሉ የማያቋርጥ ሰቆቃ እየፈፀሙበት ይገኛሉ፡፡
ሆኖም የአርማጭሆ ህዝብ የህወሓት ግድያ፣ እስር፣ ሰቆቃና ማንገላታት ሳይበግረው ለነፃነቱ እየታገለ መሰዋዕትነት መክፈሉን ቀጥሏል፡፡ የአርማጭሆ ህዝብ ሴት፣ ወንድ፣ ጎልማሳ፣ አዛውንት ሳይል አርበኞች ግንቦት ሰባትን ከመቀላቀል ነፍጥ አንስቶ በመደራጀት በአካባቢው እስከ መታገል ድረስ ተራምዷል፡፡ የአርማጭሆ ወጣቶች በየቀኑ ወደ ኤርትራ በረሃ ይጎርፋሉ፤ የአርማጭሆ ገበሬ በየቀኑ ጠብመንጃውን ወልውሎ “ጭቆና በቃኝ እምቢ አልገዛም!” በማለት በህወሓት ላይ አምፆ ይሸፍታል፤ ሸፍቶም ባገኘው አጋጣሚ ህወሓትን ከማድማት ቦዝኖ አያውቅም፡፡
አበራ ጎባው ጠብመንጃ አንስተው ለነፃነታቸው የሚታገሉ አማፂ ገበሬዎችን በማሰተባበርና በመምራት በአርማጭሆ ብቻ አይደለም ከመተማ እስከ ቋራ፣ ከጠገዴ እስከ ትግራይ ድረስ ህወሓትን በማስጨነቅ የሚታወቅ እና ለገጠሩ ጭቁን የኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ መምህር የሚሆን አይበገሬ ጀግና የፃነት ፋኖ ነው፡፡ ህወሓት አርማጭሆ ላይ እንዳሻው እንዳይንቀሳቀስ የእግር እሳት የሆነበት ጀግናው አበራ ጎባው ነው፡፡
ከጥቂት ወራት በፊት የ24ኛ ክፍለ ጦሮቹ እነ ኮሎኔል አዲሱ የተገደሉበትን የደፈጣ ጥቃት ያደረሰው ጀግናው የነፃነት ፋኖ አበራ ጎባው ነው፡፡ በላንድ ክሩዘር መኪና በፍጥነት ይጓዝ የነበረውን የህወሓት ከፍተኛ መኮንን ኮሎኔል አዲሱን እና ሌሎችን አብረውት የነበሩትን የህወሓት ወታደሮች በመግደል ከ200 ሺህ ብር በላይ ነጥቆ ለትግል ጓዶቹ አከፋፍሏል፡፡ ጀግናው የነፃነት ፋኖ አበራ ጎባው፡፡
ታላቁን የትግል መምህር አበራ ጎባውን የአርማጭሆ ህዝብ እንደ አይኑ ብሌን ነው የሚመለከተው፡፡ ህወሓት በአካባቢው በሚፈፅመው ግፍ ቆሽቱ እርር ድብን የሚለው የአርማጭሆ ሰው “አበራ ጎባው በዚህ ቦታ ይህን ያክል የህወሓት ታጣቂ ገደለ…” የሚል ዜና ሲሰማ “ቅቤ አጠጥቶ አንጀቴን አራሰው አያ! አበራ ጎባው እድሜህን ያርዝመው፤ አጅህ ወርቅ አባር ይሰር…” በማለት ይመርቀዋል፡፡ አርማጭሆዎች መርቶ እና አስተባብሮ አንድ ቀን ክህወሓት የግፍ አገዛዝ ነፃ እንደሚያወጣቸውም በእሱ ላይ ትልቅ እምነት አላቸው፡፡
ጀግናው አበራ ጎባው በአንድ መንደር ውስጥ እያለ በእንዳንድ አድር ባዮች ጥቆማ የደረሰው የህወሓት ጦር መጥቶ መንደሯን በመውረር አሰሳ ያደርጋል፡፡ በመንደሪቱ የሚኖሩ ካህናት ወደ ቤተ ክርስቲያን ወስደው ቤተ መቅደስ ውስጥ በመደበቅ እንዲያመልጥ አስችለውታል፡፡
የስነ-ልቦና የበላይነት ስላለው በአርማጭሆ፣ ቋራ እና መተማ የሚንቀሳቀሱ የህወሓት ታጣቂ ኃይሎች “የአስማት መድሃኒት ተቀብቷል…” እያሉ ያሙታል፤ ወደ ኤርትራ ተሻግሮ በቀድሞው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ ስልጠና ተሰጥቶት የተመለሰውን፣ ታላቁን የትግል መምህር፣ አይበገሬውን፣ ጀግናውን የነፃነት ፋኖ አበራ ጎባውን…

No comments:

Post a Comment

wanted officials