Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, March 10, 2016

የሰማያዊ አባላትን ጨምሮ 13 ሰዎች የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው

የሰማያዊ አባላትን ጨምሮ 13 ሰዎች የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ 13 ሰዎች ዛሬ የካቲት 27/2008 ዓ.ም በፌደራል አቃቤ ህግ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡
በጋሞ ጎፋ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አደራጅ በሆነው አቶ ሉሉ መሰለ ስም በተከፈተው የክስ መዝገብ የተካተቱት ተከሳሾች፡-
1. ሉሉ መሰለ
2. ዓለም ክንፈ
3. አየለች አበበ
4. በጋሻው ዱንጋ
5. በረከት ተገኔ
6. ደረጀ አደመ
7. ዘኪዮስ ዘሪሁን
8. ጌታሁን ቃጻ
9. ሲሳይ አምባው
10. መርዶኪዮስ ሽብሩ
11. መሀመድ ዳና
12. አጥናፉ አበራ፣ እና
13. ያረጋል ሙሉዓለም ናቸው፡፡
ተከሳሾች በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ በተሰየመው አርበኞች ግንቦት ሰባት የሽብር ድርጅት ተግባር ውስጥ ለመሳተፍ አባል ሆነው ኤርትራ ባለ የድርጅቱ አባል ትዕዛዝ መሰረት በፈጸሙት በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ በማናቸውም መልኩ በመሳተፍ የጸረ-ሽብር አዋጁን አንቀጽ 7(1) ተላልፈዋል በሚል መከሰሳቸውን የአቃቤ ህግ ክስ ያስረዳል፡፡
ተከሳሾች ከአርባ ምንጭ ከተማ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ተደርገው ከዛሬ አራት ወራት ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials