Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, March 31, 2016

በኢትዮጵያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል


መጋቢት ፳፩( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መረጃዎች እንደሚመለክቱት ከድርቅ እና ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በመቶዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች በመላ አገሪቱ በመዘጋታቸው በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ውጪ ሆነዋል፡፡ ከድርቅ ጋር በተያያዘ በርካታ ትምህርት ቤቶች ከተዘጉባቸው መካከል ሶማሊ፣ አፋር፣ ደቡብ እና አማራ ክልሎች ሲጠቀሱ፣ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ደግሞ አበዛኞቹ ትምህርት ቤቶች የተዘጉት በኦሮምያ ነው፡፡ በደቡብ በኮንሶና ሀመር ወረዳዎች፣ በአማራ በሰሜን ጎንደር አንዳንድ አካባቢዎች ከ ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ በርካታ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል።
ድርቅ ባጠቃባቸው አካባቢዎች አብዛኞቹ ተማሪዎች ትምህርት ያቁዋረጡት፣ ውሃ በመቅዳት ወላጆቻቸውን ስለሚያግዙ እንዲሁም ምግብ ፍለጋ ከውላጆቻቸው ጋር በምሰደዳቸው ነው። መምህራንም ቢሆን ትምህርት ቤቶቸን እየዘጉ ተሰደዋል። ሁኔታዎች ካልትልወጡ በቀር ተማሪዎች በዚህ አመት ትምህርታችውን ይጀምራሉ ተብሎ አይታሰብም፡
ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ደግሞ አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶቸ ይተዘጉት በመንግስት ትዛዝ ነው። በኦሮምያ የሚታየው ተቃውሞ ባለመብረዱ በርካታ ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ ሊቆዩ ይችላሉ።
በበርካታ ትምህርት ቤቶች የጸጥታ ሃይሎች የሚያደርጉት ክትትል፣ ትምህርታቸውን በጀመሩት ተማሪዎች ሳይቀር የሰነ ልቦና ጫና እየፈጠረ ነው። ትምህርት ቤቶች ተዘግተው በተከፈቱባቸው አካባቢዎች ደግሞ ተማሪዎች በደንብ ሳይማሩ ፈተና እንዲፍተኑ መደረጉን እየተቃውሙ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ በምስራቅ ሃረርጌ በፋዲስ ወረዳ እየተደረገ ያለው ተቃውሞ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎአል። ተቃዋሚዎች በመንግስት ተቁዋማት ላይ እርምጃ መውሰዳቸው ታውቁዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials