Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, March 10, 2016

የህወሃት ብሄራዊ መረጃ ከፍተኛ ሚስጥራዊ አባላት ተገደሉ!!

የህወሃት ብሄራዊ መረጃ ከፍተኛ ሚስጥራዊ አባላት ተገደሉ!!
የብሔራዊ መረጃ የቅድመ ዝግጅት ማሰራጫና ማከናወኛን ክፍል መሰረት
ባደረገ መልኩ ለመረጃ ክፍሉ ሐገር ለሐገር እየርተዘዋወሩ ሲሰልሉና ወሬ
ሲያቀብሉ እንዲሁም ያለአግባብ ወገኖቻችንን ሲያሳስሩና ሲያስገድሉ የነበሩ
አራት ቁልፍ አባላቶች መገደላቸዉን ታማኝ የመረጃ ክፍሉ ምንጫችን
ሚስጥር አዉጥተዋል። ተጠሪነታቸዉ ለመረጃዉ ክፍል ዳይሬክተር ብቻ እና
በከፍተኛ ሚስጥር ከሌሎች አባላት እንኳ በተሰወረ መልኩ የሚንቀሳቀሱ
ብዛት ያላቸዉ አባላቶች ላይ እርምጃዎቹ ያነጣጠሩ ናቸዉ ሲሉም ምንጫችን
የገለጹ ሲሆን እርምጃ የተወሰደባቸዉ ግለሰቦችን ስም ከዚህ በታች
አስቀምጠዋል ።
1. አቶ በኩር ባዘዘዉ ገብረህይወት
2. ቀሲስ ትንሳኤ ሃይለ መለኮት
3. ሲስተር ሳምራዊት በቃሉ
4. መምህር ጣፋ አጋፋሪ
በየካቲት 28/2008 ለመረጃዉ ክፍል የወረደዉ የሞት መርዶ ብዙዎችን
ያስደነገጠ ከመሆኑ ባሻገር የአራቱም ግለሰቦች አሟሟት በተመሳሳይ ወቅትና
በተለያየ ክልል መሆኑ እንዲሁም አራቱም ከተገደሉ ወዲህ ለመረጃ ክፍሉ
ካልታወቁ ግለሰቦች የስልክ ጥሪ ተደርጎ በሐገሪቷ ላይ እየተካሄደ ያለዉ
አፈናና ግድያ እስካልቆመ ድረስ እርምጃዉ እንደሚቀጥል ማስጠንቀቂያ
መሰጠቱ ዉጥረቱን አባብሶታል።
በተለይም በኦሮሚያ ክልል እና በጎንደር እንዲሁም በኦጋዴን ክልል አካባቢ
ተሰማርተዉ የነበሩ የመረጃዉ ሰራተኞች በሙሉ እርምጃ ሊወሰድባቸዉ
እንደሚችል የጠቆመዉ ምንጫችን በእነዚህ ክልል የተሰማሩ አባላቶች
ጠርገዉ እየወጡ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

(ጉድሽ ወያኔ)

No comments:

Post a Comment

wanted officials