ነቢዩ ሲራክ
በኩዌት “ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ የ23 ዓመቷን ፋጢማ የተባለችን ኩዌታዊ የአሰሪዋን ልጅ ገድላና ራሷን አቁስላለች ” በሚል በፖሊስ ጥበቃ ላለፉት ሳምንታት ሳባ በሚባል ሆስፒታል ህክምና ላይ የነበረችው ኢትዮጵያዊት ዛሬ ሐሙስ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካበቢ ማረፏን አረጋግጫለሁ ። ሆስፒታል ከገባች ጀምሮ በኩዌት ኤንባሲ ስትጠየቅ የሰነበተችው እህት ከቀናት በፊት በተሻለ ጤንነት ላይ እንደነበረች ተጠቁሟል ። በአካል ያዩዋት ወገኖች በተለይ በአንገቷ ላይ ተተክሎ የነበረው ቱቦ ተነስቶላት እንደነበርና ለመናገር ሙከራ ታደርግ እንደ ነበር አጫውተውኛል ።
በተመሳሳይ ሁኔታ ከሳምንት በፊት የተለቀቁት መረጃዎች ይህችው እህት ከጉዳቷ እንዳገገመች ተነግሮ ነበር ። ይሁን እንጅ የዛሬ ምሽት ” አሟሟቷ ከልብ ህመም ጋር በተገናኘ ነው ” የሚል መልስ በሆስፒታሉ እየተሰጠ እንደሆነ ጉዳዩን የሚከታተሉት ወገኖች መረጃውን አጋርተውኛል ! አንዳንድ መረጃውን የሰሙ ወገኖች በበኩላቸው ” በግድያው ወቅት ያን ያህል ደሟን ፈሷ ልቧ ሰከክ ሳይል እንዴት በልብ ህመም ህይዎቷ አለፈ ይባል ? ” በማለት ያጠይቃሉ!
ነፍስ ይማር !
ነቢዩ ሲራክ
የካቲት 25 ቀን 2008 ዓም
የካቲት 25 ቀን 2008 ዓም
No comments:
Post a Comment