Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, March 17, 2016

ብሄራዊ ጭቆና እንዲቆም የሚጠይቅ ተቃውሞ በአዲስ አበባ ኑር መስጊድ ተካሄደ

በእስር ላይ የሚገኙ የሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱና መንግስት እየፈጸመ ያለውን ብሄራዊ ጭቆና እንዲቆም የሚጠይቅ ተቃውሞ አርብ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው በኑር መስጊድ ተካሄደ።
ለሶስተኛ ሳምንት በተካሄደው በዚሁ ተከታታይ ተቃውሞ የሙስሊሙ ማህበረሰብ የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማትና በማውለብለብ እየደረሰብን ነው ያሉት ብሄራዊ ጭቆና እንዲያበቃ መጠየቃቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
የአርብ የጸሎት ስነ-ስርዓት ተከትሎ የተካሄደው ይኸው ተቃውሞ በእስር ላይ የሚገኙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ ጥሪን ያስተላለፉ ሲሆን የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞን ለማስቆም ሙከራ ማድረጋቸው ታውቋል።
“ብሄራዊ ጭቆናን አንሸከምም፣ ነጻነትን እንፈልጋለን” የሚሉ መፈክሮችን ያነገቡት ታዳሚዎች ሰላማዊ ጥያቄያቸው ምላሽን እስከሚያገኝ ድረስ ተቃውሞው ቀጣይ መሆኑንም ገልጸዋል።
በየሳምንቱ አርብ የሚካሄደው ልዩ የጸሎት ስነ-ስርዓት ተከትሎ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተለያዩ ስፍራዎች ተመሳሳይ ተቃውሞዎች ማካሄዳቸው ይታወሳል።
ከሶስት አመት በላይ ተቃውሞን እያቀረቡ የሚገኙት እነዚሁ አካላት የእስር ቅጣት የተለፋፈባቸውና ከ10 የሚበልጡ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከእስር እንዲፈቱ ጥያቄን ሲያቅርቡ ቆይተዋል።
ፍትህ ሚኒስቴር የተወሰኑ የኮሚቴ አባላቱን በምህረት ቢለቅም ተቃውሞን እያሰሙ የሚገኙት አካላት ሁሉም የኮሚቴው አባላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በእስር ላይ የሚገኙ ከ10 በላይ የኮሚቴው አባላት ባለፈው አመት ከሰባት እስከ 15 አመት የሚደርስ የእስር ቅጣት እንደተላለፈባቸው ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials