Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, March 11, 2016

በአማራ ክልል አስተዳደር አካላት ላይ እርምጃዎች ተወሰዱ

የመልካም አስተዳደር ችግር በፈጠሩ አካላት ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች
=======================================
በአማራ ክልል ምክር ቤት በቀረበው ሪፖርት መሰረት የመልካም አስተዳደር ችግር በፈጠሩ አካላት ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
በፍትህና ጸጥታ አካላት ላይ የተወሰዱ፡-
• 50 አመራሮች ከሀላፊነታቸው እንዲሰሱ ተደርጓል
• 2 የዞን መምሪያ ሀላፊዎች ታስረዋል
• 6 አመራሮች በህግ እንዲጠየቁ ተደርገዋል
በህብረተሰቡ አመኔታ የሌላቸውና በቂ ማስረጃ በሌላቸው የፍትህ አካላት ላይ ደግሞ ከቦታ ቦታ የማዛወር ስራ ተሰርቷል
በአስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮችና መዋቅሮች በኩል ከፖሊስ አካላት መካከል
• 16 ወደ ሌላ ቦታ ተዛውረዋል
• 18 ከስራ ታግደዋል
• 113 ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል
• 15 ለዲሲፕሊን እንዲቀርቡ ተደርጓል
• 232 ከስራ ተሰናብተዋል
• 121 ትጥቅ አውርደዋል
• 267 ከሀላፊነታቸው ወርደዋል
በሌሎች ከህብረተሰቡ የተወሰዱ እርምጃዎች
• በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ በመከሩ 76 ሰዎች ላይ ክስ ተመስርቷል
• በወልድያ ከተማ 12 አራጣ አበዳሪዎች ላይ ክስ ተመስርቷል ሀብታቸውም ታግዷል
• በአዊ ብሄረሰብ በአራጣ አበዳሪዎች የወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው 5 መዝገቦች እንዲቋረጡ ተደርጓል
• ከ10 ያላነሱ ጉዳዮች በእርቅ እንዲቋጩ ተደርጓል
• ከዓመት በፊት ንብረታቸውን አስረክበው የተሰደዱ ወደ 6 የሚደርሱ ግለሰቦች ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ ተደርጓል
• በምዕራብ ጎጃም ዞን በ40 የአራጣ አበዳሪዎች ላይ የወንጀል ምርመራ እየጣራባቸው ነው
ከንግድ ስርዓቱ ጋር
• 12 ግለሰቦች ከስራ ላይ የስራ ስንብት ፣የደመወዝ ቅጣት፣የእርከን ዝቅታ እና በፍርድ ቤት የመክሰስ ህጋዊ ና አስተዳደራዊ እርምጃዎች ተወስዶባቸዋል
ከመንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ የስነ ምግባር ችግር በታየባቸው 35 ሙያተኞች ላይ እርምጃ ተወስዷል
342 ባለሀብቶች በትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ህግ የተላለፉ ተቀጥተዋል፡፡
ከግብረ ጋር በተያያዘ
• 12 ግለሰቦች ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ ተወስዷል
• 17 የታክስ ወንጀል በፈጸሙ ባለሀብቶች ላይ ክስ ተመስርቶ 5ቱ ተቀጥተዋል ብለዋል ርዕሰ መስተዳደር የተከበሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፡፡
አብመድ

No comments:

Post a Comment

wanted officials