የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች አሜሪካ ኢምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ተሰማ
ኢሳት (የካቲት 29 ፥ 2008)
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች በኦሮሚያ ክልል የሚፈፅሙትን የሃይል እርምጃ በመቃወም ማክሰኞ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ።
ያልተጠበቀ ነው የተባለውን ሰላማዊ ሰልፍ አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ያካሄዱት ተማሪዎች የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞን በሚያሰሙ ነዋሪዎች ላይ እየወሰዱ ያለውን የሃይል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ መጠየቃቸውም ታውቋል።
ተማሪዎቹ ጥያቄያቸው ሰላማዊ እንደሆነ ለማሳየት ነጭ ጨርቅን እያውለበለቡ ጥያቄያቸውን ቢያቀርቡም በጸጥታ ሃይሎች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ተማሪዎቹ ለሮይተርስ ገልጸዋል።
ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን ለመግለጽ ያልፈለጉ ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፉ በኦሮሚያ ክልል እየተፈጸመ ያለው ግድያና እስራት ትኩረት እንዲያገኝ መሆኑ ለዜና አውታሩ አስረድተዋል።
ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አራተኛ ወሩን ያስቆጠረ ሲሆን የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ማክሰኞ ያካሄዱት ሰልፍ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑንም ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎም ቁጥራቸው በትክክል ያልታወቁ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተነግሯል።በኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው ግድያ ይቁም የሚል መፈክር በመያዝና ነጭ ጨርቅ በማውለብለብ ወደ አሜሪካ ኢምባሲ ያመሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ፣ በአካባቢው ሲደርሱ በፖሊሶች ተደብድበዋል።
ተማሪዎቹ “እኛ አሸባሪዎች አይደለንም፣ ግድያው ይቁም!” የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል። ፖሊሶች በተማሪዎች ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን ተከትሎ ተማሪዎች ቢበታተኑም፣ ፖሊሶቹ ግን ተቃውሞውን አስተባብረዋል ያሉዋቸውን ይዘው በማሰር ላይ ናቸው።
በወለጋ ዩኒቨርስቲ ፖሊሶች በተማሪዎች መኝታ ከፍሎች ውስጥ ገብተው ባደረሱት ድብደባ በርካታ ተማሪዎች ተጎድተው ሆስፒታል መተኛታቸውም ታውቋል።

ይሁንና የመንግስት ባለስልጣናት በጉዳዩ ዙሪያ የሰጡት ምላሽ አለመኖሩን ሮይተርስ በዘገባው አስፍሯል።
No comments:
Post a Comment