Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, March 12, 2016

በኦሮምያ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ በውጭ ሃይሎች የተፈጠረ አይደለም ሲሉ ጠ/ሚኒስትሩ ተናገሩ

በኦሮምያ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ በውጭ ሃይሎች የተፈጠረ አይደለም ሲሉ ጠ/ሚኒስትሩ ተናገሩ

የካቲት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከኦል አፍሪካ ጋዜጠኛ ሪድ ክራመር ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ዘጋርድያን ይዞት የወጣ ሲሆን፣ ጠ/ሚኒስትሩ በኦሮምያ የሚታየው የህዝብ ተቃውሞ ከስራ አጥነት እና ከመሬት ዝርፊያ ጋር የተያያዘ እንጅ የውጭ ተጽእኖ የለበትም ብለዋል። የስራ አጡ ቁጥር 16 በመቶ በላይ መድረሱን፣ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው እድሜው ከ30 አመት በታች መገኘቱን የገለጹት አቶ ሃይለማርያም፣ ለዚህ ሁሉ ወጣት ስራ መፍጠር በሚገባን ልክ ለመፍጠር ባለመቻላችን የተፈጠረ ተቃውሞ ነው ብለዋል። ሌላው ምክንያት በከተሞች የሚታየው የመሬት ዝርፊያ፣ አርሶ አደሩን በማፈናቀሉ የተፈጠረ ችግር ነው ያሉት አቶ ሃይለማርያም ፣ የግጭቱ መሰረታዊ ችግር ስራ አጥነትና የመልካም አስተዳደር ችግር መሆኑን ተገንዝበናል ብለዋል።
ይህ አባባላቸው ከዚህ ቀድም እርሳቸውም ሆኑ የኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ ከአመጹ ጀርባ ሻእቢያና በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ድርጅቶች እጅ አለበት በማለት ሲሰጡ ከነበረው መግለጫ ጋር ሙሉ በሙሉ የሚጋጭ ነው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials