(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) የወልቃይቱ ታዋቂ ባለሀብት የሆኑት አቶ ሹምዬ ገብሩ በትናንትናው ዕለት ተመርዘው ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ፡፡
አቶ ሹምዬ ገብሩ በእርሻው እና በንግዱ ዘርፍ በጎንደር ከተማ እና አካባቢው፣ ወልቃይት፣ እንዲሁም አርማጭሆን ጨምሮ ደህና የሚንቀሳቀሱ ነብስ ያላቸው ሀብታም ነጋዴ ነበሩ፡፡

ትናንት የካቲት 7/07/2008 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ለስራ ወዲያ ወዲህ በሚሯሯጡበት ጊዜ በበሉት ምግብና
መጠጥ አካላቸው ተመርዞ ወደ ህክምና ቢወሰዱም በተደረገላቸው እርዳታ በህይወት ሊተርፉ ባለመቻላቸው ሳይታሰብ
በድንገት ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
አቶ ሹምዬ ገብሩ በአሁኑ ወቅት እየከረረ መጥቶ ከጫፍ የደረሰው የወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ዋነኛ አቀንቃኝ ከመሆናቸው ባለፈ ለኮሚቴው ያልተቋረጠ የገንዘብ፣ የሀሳብና የሞራል ድጋፍ ሲያደርጉ የቆዩ ናቸው ተብሏል፡፡
ስለሆነም በአቶ ሹምዬ ገብሩ በምግብ ተመርዞ በድንገት ለህልፈት መብቃት የህወሓት አገዛዝ ስውር አጅ እንዳለበት ፍንጭ የሚሰጡ መረጃዎች እንዳሉ ዜናውን ያደረሱን ምንጮች ገልፀዋል፡፡

No comments:
Post a Comment