Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, March 11, 2016

አምስት የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት በኢትዮጵያ ጉዳይ ለፕሬዝዳንት ኦባማ ደብዳቤ ጻፈ


አሉላ ከበደ

“በተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎች የሚፈጸመው አፈና አሳስቦናል።” አምስት የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ለፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የጻፉት ደብዳቤ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
አምስት የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት አንድ በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የጋምቤላ አስተዳዳሪእንዲለቀቁ፤ የጠየቁበትን ደብዳቤ በትላንትናው ዕለት ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ላኩ።
የምክር ቤት አባላቱ በኢትዮጵያ ይፈጸማል ያሉት የፖለቲካ መሪዎች አፈና እንዲያቆም ኦባማ ግፊት ያደርጉዘንድ ጠይቀዋል።
ላለፉት ሁለት ዓመታት በፖለቲካ እስርኝነት እየማቀቁ ነው ያሏቸው የቀድሞው የጋምቤላ አስተዳዳሪ አቶ ኦኬሎአክዌይ ይለቀቁ ዘንድ ፕሬዝዳንት ኦባማን የጠየቁበትን ደብዳቤ የጻፉት፤ የመካከለኛው ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትሷ የሜነሶታ ክፍለ ግዛት እንደራሴዎች ሪክ ኖላን (Rick Nolan) ፣ ኪት ኤሊሰን (Keith Ellison) እና ቤቲ መኮለም (Betty McCollum) እንዲሁም የፍሎሪዳ ክፍለ ግዛቱ አልሲ ሃስቲንግስ (Alcee Hastings) እና የሮድ አይላንዱ ወኪል ዴቪድ ሲሲሊን (David N. Cicilline) ናቸው። አምስቱም የዲሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ናቸው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials