Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, March 1, 2016

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በታክሲዎች አድማ ምክንያት ተሰረዘ

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በታክሲዎች አድማ ምክንያት ተሰረዘ

የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት 120ኛውን የአድዋ ድል በዓል በነገው እለት ለማካሄድ የያዘውን የፖናል ውይይት ከአ/አ ታክሲዎች አመጽ ጋር በተያያዘ ለመሰረዝ ተገዷል።
ጽ/ቤቱ የካቲት 22 ቀን 2008 ዓ.ም በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል የፖናል ውይይቱን ለማካሄድ አቅዶ ለሆቴሉ ክፍያ የፈጸመውና ለተሳታፊዎች ጥሪ ያስተላለፈው ከሳምንት በፊት ነበር። ሆኖም በአ/አ ከተማ በመካሄድ ላይ ያለው የታክሲ ሹፌሮችና ባለንብረቶች አመጽ በነገው እለትም ይቀጥላል በሚል ምክንያት ፕሮግራሙ ተሰርዟል።
በፖናል ውይይቱ ላይ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተጋብዘው የነበረ ሲሆን፣ ከ120 አመታት በፊት ጀግኖች አባቶቻችን በጠላት ላይ ያደረጉት ተጋድሎን ወጣቱ ትውልድ በድህነት ላይ ሊደግመው ይገባል በሚል የፖሮፖጋንዳ ጥናታዊ ጽሁፎች ተዘጋጅተው እንደነበር ከጽ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል

No comments:

Post a Comment

wanted officials