Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, March 30, 2016

የሰዋስወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ ኮሌጅ: በኑፋቄ ተግባር ያገኘውን ደቀ መዝሙር አባረረ፤ የሦስት ተጨማሪ ደቀ መዛሙርት ጉዳይ እየታየ ነው


ውሳኔውን፥ በሽምግልና፣ በዛቻና በማስፈራራት ለመቀልበስ እየተሯሯጠ ነው
የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ፥ ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት፣ ሥርዐትና ትውፊት ውጭ ኑፋቄን ሲያስፋፋና ሲተገብር በተጨባጭ አግኝቸዋለኹ፤ ያለውን አንድ ደቀ መዝሙር ከኮሌጁ ማሰናበቱ ተገለጸ፡፡
ከፍ ያለው ቱፋ የተባለው ግለሰብ፣ በቀን ተመላላሽ የሦስተኛ ዓመት ሰሚነሪ ደቀ መዝሙር ሲኾን፤ በኮሌጁ ውስጥ በኅቡእ ኑፋቄን ሲያስፋፋና በቅጥረኛነትም ከኮሌጁ ወደ መናፍቃን ጎራ አንዳንድ ደቀ መዛሙርትን እየመለመለ ሲቀሥጥና ሲያስኮበልል መቆየቱ ተጠቅሷል፡፡
በኮሌጁ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የሚመራ፥ የአስተዳደር፣ የመምህራንና የደቀ መዛሙርት መማክርት ጉባኤ÷ መጋቢት 16 ቀን ባካሔደው ስብሰባ፣ የመናፍቃን ቅጥረኛ ኾኖ በሚንቀሳቀሰው ደቀ መዝሙር ላይ ሲሰበሰቡ የቆዩ ማስረጃዎችን ከመረመረና ደቀ መዝሙሩንም አቅርቦ ከጠየቀ በኋላ ከኮሌጁ ጨርሶ እንዲሰናበት ልዩነት በሌለው ድምፅ መወሰኑ ታውቋል- “ከመጋቢት 19 ቀን ጀምሮ በኮሌጁ እስከ መጨረሻው እንዳይማሩ ተሰናብተዋል” ይላል፤ ዛሬ ከቀትር በኋላ ከአስተዳደር ዲኑ ቢሮ የወጣው ደብዳቤ፡፡
ppp
የኮሌጁ አካዳሚክ ምክትል ዲንና የጥበቃ ክፍል ሓላፊ የደቀ መዝሙሩን መታወቂያ በመቀበል ውሳኔውን እንዲያስፈጽሙ በደብዳቤው ግልባጭ የታዘዙ ሲኾን፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት፣ የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ርምጃውን እንዲያውቁት ተደርጓል፡፡
በሌላ በኩል፣ ኮሌጁ የሃይማኖት ሕጸጽ የተገኘባቸውን ተጨማሪ ኹለት ደቀ መዛሙርትና ከፍተኛ የሥነ ምግባር ጉድለት የተገኘበትን አንድ ደቀ መዝሙር ጉዳይ እየመረመረ ሲኾን እገዳን ጨምሮ ቀኖናዊ ቅጣት ሊተላለፍባቸው እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ ከእኒኽም አንዳንዶቹ፣ በኮሌጁ በማታው ክፍለ ጊዜ የሚማሩትን እንደ ዘካርያስ ሐዲስ ያሉ የለየላቸውን አማሳኞች ባካተተ ሽምግልና እንዲኹም፤ በሓላፊዎቹ ላይ በመዛትና በማስፈራራት ውሳኔውን ለማስቀልበስ እየተሯሯጡ እንዳሉም ተሰምቷል፡፡
ለጥንታዊው የአብነት ትምህርት ትኩረት የሚሰጠው አንጋፋው ኮሌጅ፣ በቀንና በማታው ክፍለ ጊዜ ከ800 በላይ ደቀ መዛሙርትን ተቀብሎ በመጻሕፍት ትርጓሜያትና በሴሚነሪ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡
ምንጭ፦ ሐራ ዘተዋህዶ

No comments:

Post a Comment

wanted officials