Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, March 13, 2016

በኢትዮጵያ በፕሬስ ነጻነትና በተቃዋሚዎች ላይ የሚደርገው ጫና እንደሚያሳስባት ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች






ማርች 12, 2016
አሉላ ከበደ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት
“የንግግር ነጻነትን በማረጋግጥና ዲሞክራሲያዊ እርምጃዎችን በማጎልበት የኢትዮጵያ መንግስት ቀደም ሲል የወሰዳቸውን አዎንታዊ እርምጃዎች እንዲያጠናክ እያሳሰብን፤ በነጻ ድምጾች ላይ የሚፈጸመው አፈና ይህን መሰሉን አዎንታዊ እርምጃ ማደናቀፍ ብቻ ሳይሆን፤ የልማትና የምጣኔ ሃብት እድገትንም የሚገታ መሆኑን መጠቆም እንፈልጋለን።” የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያ በፕሬስ ነጻነት ላይ የሚደረገው ገደብና የጸረ ሽብር ሕጉን በመጠቀም መንግስት በጋዜጠኞች፥በመብት ተሟጋቾችና በተቃዋሚዎች ላይ የሚያደርገው ጫና የሚያሳስባት መሆኑን ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች።

በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የጋምቤላ አስተዳዳሪ እንዲለቀቁና በኢትዮጵያ የዜጎች መሠረታዊ መብቶችእንዲከበሩ በመጠየቅ አምስት የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ከትላንት በስቲያ ለፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማየጻፉትን ደብዳቤ ተንተርሶ ለቀረቡ ጥያቄዎች በሰጠው ምላሽ ነው፤ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ይህንያለው።

በሌላ ተያያዥ ዜና፤ የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮምያ ክልል በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የወሰደው የኃይል ዕርምጃአሳስቦናል፤ ሲሉ አንዲት የመካከለኛው ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትሷ የሜነሶታ ክፍለ ግዛት የምክር ቤት አባል ለግዛቲቱሸንጎ ባቀረቡት ረቂቅ አመልክተዋል።





No comments:

Post a Comment

wanted officials