Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, March 25, 2016

ጎንደር የዘር ጦርነት አደጋ ተጋርጧል፥

ጎንደር የዘር ጦርነት አደጋ ተጋርጧል፥
የወልቃይት ጠገዴ ሚሊሻ ሰራዊትና ጸረ-ሽምቅ ታጣቂዎች ከህዝቡ እንደሚወግኑ በመስጋት ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ጥሪ ተደርጎላቸዋል፥ እነዚህ ታጣቂዎች ግን በዚህ ሰዓት ትጥቅ መፍታት ዘበት ነው ብለዋል፥ ብዙ ወጣቶች ከእነሙሉ ትጥቃቸው ጫካ እየገቡ ነው፡፡
የወልቃይት ጠገዴ የዳንሻና የዓካባቢው ወጣቶች ወደ አርማጭሆ ወረዳዎች፥ ሶሮቃ፣ አብራጅራ፣ አብደራፊና ሳንጃ እየከተቱ ነው፥ የአርማጭሆ ወጣትም የጀግና አቀባበል እያደረጉላቸው ነው፡፡
የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ያገታችኋቸውን ባሎቻችንና ልጆቻችንን ልቀቁ በማለት በዳንሻ ዓደባባይ ወጥተዋል፥ የሕወሓትን ሽምቅ ተዋጊ ኃይል ግብግብ ገጥመዋል፥ በበርበሬ ብጥብጥ ዓይናቸውን እያጠፉ ትጥቅ መማረክ ጀምረዋል፡፡
ባለፈው ዓመት ግጨውና ሶሮቃ የአርማጭሆና የሕወሓት ሚሊሻ ውጊያ ማድረጉ ይታወሳል፥ ዓሁንም ወደዚህ ዓካባቢ ካላይ ዓርማጭሆና ከምዕራብ ዓርማጭሆ፣ ከወገራ እስከ መተማና ሽንፋ ክተት ብሎ ወደ ሶሮቃ እያመራ ነው፥
ከሰሜን ጎንደር ዓልፎ፥ ከአቸፈር፣ ከዳሞት፣ ከቋሪት፣ ከደብረ ታቦር፣ ከጋይንት፣ ከበለሳ፣ ከዋግና ከጎባ ላፍቶ ወደ ጠገዴና ወልቃይት የሚጓዘው ሕዝብ መበራከታቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ይህ የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ፥ የጎንደር ሕዝብ ብቻ ዓይደለም፥ ጥያቄው የኢትዮጵያውያን ሁሉ መሆኑን በመገንዘብ እያንዳንዱ ዜጋ ሊሳተፍበት ይገባል፥ ጉዳዩ የመላው አማራ ሕዝብ ቢሆንም፥ አገራችን ኢትዮጵያን የተቆጣጠረው የትግራይ-ወያኔ ድርጅት ከሥልጣን እስካልተወገደ ድረስ መፍትሄ ሊገኝለት የማይችል የዲሞክራሲና የፍትህ ጥያቄ ነው፥
ስለዚህ በኦሮሞ ወገኖቻችን ችግር ጊዜ እንደታየው ሁሉ፥ በወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ግፍ መላው ኢትዮጵያዊ ማውገዝ አለበት፡፡

 

No comments:

Post a Comment

wanted officials