Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, March 16, 2016

በዱባይ የታሰሩት ነጋዴዎች ቤተሰቦች መንግስት እንደረሳቸው ተናገሩ

በዱባይ የታሰሩት ነጋዴዎች ቤተሰቦች መንግስት እንደረሳቸው ተናገሩ


መጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከየካቲት 13 እስከ 17 ቀን 2008 በዱባይ “ገልፍ ፉድ ፌር ኤግዚቢሽን” ላይ ለመካፈል ሄደው ተከሰው ከሀገር እንዳይወጡ የተበየነባቸውን ስጋ ላኪ ባለሀብቶች፣ የኢትዮጵያ መንግስት በፍጥነት ጣልቃ ገብቶ ማስለቀቅ አለመቻሉ እንዳሳዘናቸው ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።
ስድስት ያህል የሚሆኑት ታሳሪ ባለሀብቶች ቤተሰቦች እንደተናገሩት ኤግዚቢሽኑ በሚካሄድበት ወቅት አንድ ጥራት የሌለው የስጋ ምርት ሸጠውልኝ ለኪሳራ ዳርገውኛል ያለ የዱባይ ኩባንያ ባቀረበው የክስ አቤቱታ መሰረት ባለሀብቶቹ ራሳቸውን እንዲከላከሉ እንኩዋን ሳይፈቀድላቸው ለእስር ተዳርገው ፖስፖርታቸውን አስይዘው መውጣታቸውን፣አንዳንዶቹ እስሩን በመፍራት መደበቃቸውን የገለጹ ሲሆን ሁሉም ተከሳሾች ከሀገር እንዳይወጡ ተወስኖባቸው በዱባይ ከ17 ቀናት በላይ እንደሆናቸው ተናግረዋል።
ጉዳዩ በንግድ ውል መሰረት መታየት ያለበትና የዱባዩም ኩባንያ ግዥ ሲፈጽም አለመግባባት ቢፈጠር በኢትዮጵያ ህግ ለመዳኘት ተስማምቶ ውል በፈረመበት ሁኔታ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬት መንግስት ጣልቃ ገብቶ ሰው ወደማሰር መግባቱ ህገወጥ መሆኑን በስጋ ላኪዎች ማህበር አማካይነት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ችግሩን እንዲፈቱ አቤቱታ ቢቀርብላቸውም እስካሁን መልስ አላገኙም። በዚህ ምክንያት ቤተሰቦቻቸው በሰው ሀገር ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት ከመዳረጋቸውም በተጨማሪ ያሉበት ሁኔታ ለደህንነታቸውም አስጊ መሆኑን መግለጻቸውን የአዲስ አበባው ዘጋቢ ተናግሯል።
የዱባዩ ኩባንያ ከስድስት ወራት በፊት ከ260 ሺ ኪሎግራም በላይ የስጋ ምርት ከስምንት የኢትዮጵያ ላኪዎች ለገዛበት ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር በላይ የከፈለ ሲሆን፣ በወቅቱ ስጋው ተበላሽቷል የሚል ቅሬታ አቅርቦ ነበር።

No comments:

Post a Comment

wanted officials