Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, October 22, 2016

የአማራ ክልል ካርታ ከሱዳን ጋር እንደማይወሰን ያመላከተው የ10ኛ ክፍል መማሪያ መጽሐፍ መታተሙ አወዛጋቢ ሆነ።

የአማራ ክልል ካርታ  ከሱዳን ጋር እንደማይወሰን ያመላከተው የ 10ኛ  ክፍል  መማሪያ መጽሐፍ   መታተሙ አወዛጋቢ ሆነ።
ለ 2009 የትምህርት ዘመን ተብሎ የታተመው የሀኤ የስነዘጋና ስነምግባር መጻሕፍ ግድፈት የክልሎችን ትክክለኛ ካርታ ስላልሆነ  እንዲታረም ከመጠየቅ ይልቅ  የሚመለከተው የትምህርት ዝግጅት ክፍል መጽሐፍጡ ከመሰራቸታቸው በፊት ግድፈቱ የታተመበት የየመጽሐፉ ገጽ 23 እና 24 ተቀዶ እንዲሰራጭ አሳስቦአል።
ይህ ከዚህ በታች የምታዩት አዲስ የመሬት ስሪት እንደሚያሳየን ፣ በቤኒ ሻንጉል ህዝብ ባርነት እና የአማራ ክልል እያደረ መኮሰስ እና ጨርሶ መጥፋት ላይ የተመሰረተ ፣ የአዲስ መሬት ባለቤቶች እና ተጠማኝ ብዙሀንን ሊፈጥር እያሴረ ነው። አገራችሁን የምትወዱ ሰዎች በፅሞና ተመልከቱት።


በጎጠኝነት ስም ቢጠሯቸው የማይሰሙት ዲታዎች ፣ አዲስ መሳፍንቶች ፣ ኢትዮጵያን የመበተን የመሀንዲስ ስራቸውን ይፋ እያደረጉ ነው። ይህ ጊዜ አደገኛ ነው። አንድ ሆነን መቆም ያለብን ወቅት ነው። በሀይማኖት በዘር እና በቋንቋ ተለያይተን የምንነታረክበት ሰአት አይደለም። አማራው ይለምልም፣ ትግሬው ይመንደግ ፣ ኦሮሞው ይፋፋ እያልን ማሾፋችን የትም አያደርሰንም።
ህዝብ የግፈኞችን አላማ ፣ በውል ሳያውቀው እና ሳይረዳ ፣ ሌሎች ህዝቦች ላይ የሚፈፀምን እልቂት የሚያራምድበት ጊዜ አለ።ባንባገነኖች ጥላ ስር የሚኖሩ ህዝቦች እነሱ ከሚያቁት አለም ውጭ የሚኖሩ ስዎች ሁሉ በላይ የታፈኑ ናቸው። ዛሬ ትግራይ የአፍሪካ ገነት ሆናለች ብሎ ማመን በጣም የተሳሳተ አመለካከት ነው። በእኔ እምነት የወያኔ ጦረኞች ከ አለም አቀፍ ወንጀለኛ የማፍያ ድርጅት ተለይተው ሊታዩ አይገባም። የሟቹ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና አሁንም በህይወት ያለው ከፍተኝ የወያኔ ባለስልጣን አቶ ስብሀት ነጋ ንብረት ብቻ ባንድ ላይ ከ 7 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ይገመታል። ይህ እኔ ፈጥሬ የማወራው ነገር አይደለም። በግልፅ የህዝቦች ሰነድ(public records) የተመዘገበ ነው። ሌላው ቀርቶ የአለቅላቂው የበረከት ስምኦን ሀብት እንኳን በ 200 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ይገመታል።ይህ የሚያሳየው የወያኔ ወሮበሎች ከሀቀኛ እና ከእውነተኛ ትግራውያን ይልቅ ከሀዲ ኤርትራውያንን እንደሚመርጡ ነው። ከኢትዮጵያ ተቆርሶ ለሱዳን የሚሰጠው መሬትም እንደሚያሳየን ፣ የወያኔ ጦር የመሸገው ፣ የዘመኑን መሳፍንቶች የደለበ ካፒታል ደህንነት እንጅ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማስከበር እንዳልሆነ ነው። የምእራባውያንን የገንዘብ ችሮታ ፍለጋ ድንበራቸውን ተሻግረው ሶማሌ ውስጥ እየተዋጉ ነው። ለዚህ አይን ያወጣ ጣልቃ ገብነት የተሰጠ አንድም ምክንያት የለም። እውቱተ ግን ይህ መንግስት፣ ምእራብ አሮራፓን እና የአሜሪክካንን መንግስት ጥቅም እያስጠበቀ ለራሱ በሚደርሰው ፍርፋሪ የበለፀገ ከሀዲ ቡችላ ነው። ጉድጓድ ውስጥ እንዳሰደጉትም ውሻ ሆኗል። ያገኘውን ሁሉ መንከስ ነው የሚልፈገው። ትግሬም ሆንክ አማራ ፣ ጉራጌም ይባል ኦሮሞ ፣ ሁሉም በኢትዮጵያዊነት የቆመ ሁሉ ላይ ነው ያተኮረው። በራሱ አምሳል ጠፍጥፎ ከሰራቸው ድርጂቶች በቀር ከጎኑ የቆመ አንድም የፓለቲካም ይሁን ህዝባዊ ተቋም የለም። ይህን መቋቋም የምንችለው በሀገር አቀፍ ሀያል እምቢተኝነት ብቻ ነው።
አለም አፍቀ ወንጀለኞችን በሰላማዊ መንገድም ይሁን በታጠቀ ህዝባዊ ሀይል ፣ ለኛ በሚመቸን መንገድ ሁሉ በተባበረ የህዝብ ክንድ መትመም ያለበትን ትግል ፣ በጎጠኛ ፖሊሲ እናሸንፈዋለን ማለት ከወሬ ያለፈ ቁምነገር የለውም። ህዝባችን ሆ ብሎ ተነስቷል። እንከተለው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials