Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, October 20, 2016

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን መንግስትን አስጠነቀቁ ።በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ውይይት እንዲደረግ ተጠየቀ



በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የደነገገው የኢትዮጵያ መንግስት «መሠረታዊ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃን» እንዲያረጋግጥ ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን አስጠነቀቁ። ዋና ጸሐፊው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተደነገገበት ጊዜ አንስቶ በኢትዮጵያ እየተከሰተ ያለውን ነገር «በጥልቅ» እየተከታተሉ መኾናቸውን የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱያሪች ትናንት አስታውቀዋል። የተመድ ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን «ሁሉንም ቅሬታዎች ለመፍታት ሁሉን አቀፍ ውይይት» እንዲደረግ ጥሪ አስተላልፈዋል። ባለፈው ቅዳሜ ይፋ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የአፈጻጸም መመሪያ፦ «ሽብርተኞች» ተብለው በመንግስት ከተጠቀሱ ማናቸውም ቡድኖች ጋር የሚደረግ ግንኙነትን ይከለክላል። ከኢትዮጵያ አጠቃላይ ነዋሪዎች 60 በመቶ ይሆናሉ ያላቸው የአማራ እና የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት ለአንድ ዓመት ግድም ተቃውሞ በማድረግ ላይ መሆናቸውን የጠቀሰው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ኤኤፍፒ የሀገሪቱ መንግስት በአብዛኛው በአናሳ የትግራይ ተወላጆች የተዋቀረ መሆኑንም አክሎ ዘግቧል።Ban Ki-moon

No comments:

Post a Comment

wanted officials