አራት የፖለቲካ ድርጅቶች ወያኔን ለመታገል የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ የተሰኘ የጋራ ንቅናቄ መመስረታቸው ይፋ ሆነ፡፡ እነዚህም አርበኞች ግንቦት ሰባት የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፡ የኦሮሞ ዶሞክራሲያዊ ንቅናቄ፡ የአፋር ህዝብ ፓርቲና የሲዳማ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሲሆኑ ምስረታውን አስመልክቶም በመጪው እሁድ ኦክቶበር 30/2016 መሪዎቹ በሚገኙበት በዋሽንግተን ዲሲ የፊርማ ስነ-ስርአት እንደሚደረግ ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄን ምስረታን አስመልክቶም በመጪው በዋሽንግንወ ዲሲ በሚደረገው የፊርማ ስነ-ስርአት ላይ ለመገኘትም የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ሊ/መንበር የሆኑት አቶ ሌንጮ ለታና ም/ሊ/መንበር የሆኑት አቶ ዲማ ነገዎ እንዲሁም የአፋር ህዝብ ፓርቲ ሊ/መንበር የሆኑት ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ አሜሪካ መግባታቸው ሲታወቅ የሲዳማ ህዝብ ዲሞክራሲያው ንቅናቄ ሊ/መንበር የሆኑት አቶ በቀለ ዋዩ በቅርቡ አሜሪካ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡
የአዲሱን ንቅናቄ ምስረታን በይፋ በሚያበስረውና እሁድ በዋሽንግተን ዲሲ በሚደረገው የመሪዎቹ የፊርማ ስነ-ስርአት ላይ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ሊ/መንበር ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ እንደሚገኙ የሚጠበቅ ሲሆን ዜናውን እስከአጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ አሜሪካ መግባታቸው ያለመታወቁን ዜናው ጨምሮ ሲያስረዳ ከፊርማው ስነ-ስርአት በተጨማሪ አራቱም የአራቱም መሪዎች በተገኙበት ህዝባዊ ጉባኤ እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል፡፡
No comments:
Post a Comment