Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, October 11, 2016

የኢትዮጵያ ሕዝብ የነጻነት ትግል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አይደናቀፍም!!!







ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም የሚገዛው ህወሃት ላለፉት 25ዓመታት መብት በገፍ ሲሰጥ የቆየ ይመስል ህገመንግሥታዊ መብቶችን የሚገፍ ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል። አዋጁ ለስድስት ወር ይቆያል ማለቱ የህወሃት ዕድሜ ከስድስት ወር እንደማይቆይ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል፡፡

ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የማንኛውም ሰው ቤት ፣ንብረት ይበረበራል ።

~ ይበልጥ ከ1997 ወዲህ እና በተለይ ማህበራዊ ሚዲያዎችን መጠቀም ከጀመርን ጊዜ አንስቶ ቤታችን እንዳሻቸው ባሻቸው ሰዓት እየመጡ በርብረው እንደሚሄዱ የአደባባይ ሚስጥ ነው ።

~ ላለፉት 25 ዓመታት መቼ ፋቅዳችሁልን የምታውቁትን ቅስቀሳ ነው የምትከለክሉን ።

ጽሁፍ ማዘጋጀት ፤ ማተምና ማሰራጨት ክልክል ነው ።

~ ላለፉት 25 ዓመታት ሀገራችን ያፈራቻቸው ድንቅ ምሁራን የሚወዷት ሀገራቸውን ጥለው የተሰደዱት ለምን ፃፋችሁ ተብለው ሰብዓዊ መብታቸው ስለተገፈፈ ነው ። ለምን ፃፋችሁ ተብለው ነው ጋዜጠኞቻችን በየ እስር ቤቱ እየተሰቃዩ ያሉት ። ስለዚህ ላለፉት 25 ዓመታት ያልፈቀዱልንን መፃፍ ነው ዛሬ ላይ የሚከለክሉን ።

በምልክት ተቃውሞ መግለፅ ክልክል ነው ።

~ በ1997 የቅንጅት ምልክት የሆነውን ሁለት ጣት ምልክት ማሳየት ሀራም ነው ብላችሁ ስታስሩን ስትደበድቡን ነበር ይባስ ብሎ መለስ ዜናዊ በአደባባይ እምቢ ካሉ ሁለት ጣታቸውን መቁረጥ ነው ብሎ ነበር ። በቅርቡም ብዙ ወንድሞቻችን በምልክት ተቃውሞ አሳይታችኋል ተብላው እየታሰሩ ነው ። እኮ መቼ ፋቅደውልን የሚያውቁትን ነው ዛሬ ላይ የሚከለክሉን ።

የተቃውሞ መልዕክት በማንኛውም መንገድ ለህዝብ ይፋ ማድረግ ክልክል ነው ።

~ ላለፉት 25 ዓመታት ፋሽስቱ የትግራይ ነፃ አውጪ ቡድን አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባ የመጀመሪያ ስራው የተለያየ አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች መረጃ እንዳይለዋወጡ የመረጃ መረቦችን መበጣጠስ ነው ። በቀጣይነትም እነ ትዊተር እና ፌስ ቡክን ያግዳል ። እስከዛሬም በሚሊየን ዶላር የሚቆጠር የሀገር ሀብት እየከፈለ ሀክ ሲያስደርግ ነበር ። ታዲያ መቼ መልዕክት እንድንለዋወጥ ፈቅዶልን የሚያውቀውን ነው አሁን የሚከለክለን ።

ላለፉት 25 ዓመታት ምንም ነገር ባላገኘንበት በአስኳይ ጊዜ አዋጁ ምንም ነገር አናጣም ።

ድል ለሰፊው ህዝብ

No comments:

Post a Comment

wanted officials