Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, October 8, 2016

የጭልጋ (አይከል) – ዙፋን – አንገረብ አዲስ መንገድ እና የህወሓት/ኢህአዴግ ድብቅ ሴራ!

የጭልጋ (አይከል) – ዙፋን – አንገረብ አዲስ መንገድ እና የህወሓት/ኢህአዴግ ድብቅ ሴራ! [በክብሩይስፋ ሲ. እና ሳጅን የሮሱን]



ከአይከል (ጭልጋ) – ዙፋን – አንገረብ ወይም ምዕራብ አርማጭሆ (አብርሃጅራ እና አብደራፊ) ወደ 2 ቢሊዮን በሚጠጋ በጀት በሱር ኮንስትራክሽን ድርጀት የአስፋልት መንገድ እንደሚሰራ የመንግስት ልሳናት በመስከረም 27 መዘገባቸው ይታወቃል፡፡ ከዘገባዎቹ መረዳት እንደሚቻለው፣ የሚገነባው የአስፓልት መንገድ አላማው የወረዳውን ቀበሌዎች ማገናኘት ሲሆን መንገዱም ደረጃውን የጠበቀና ከገጠር መንገድነት በጣም ከፍ ያለ እንደሚሆን ነው፡፡ ይሁን እንጂ ነባራዊ ሁኔታዎችን በመንተራስ ለአስፓልት መንገዱ መገንባት በመንግሰት በኩል የተሰጡት ምክንያቶች ውሃ የማያነሱና ስውር አላማን ያነገቡ እንደሆነ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡ ይህን ጹሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ የሚከተሉት እውነታዎች ናቸው፡፡
14620072_1455728487777033_521967231_n-png
• የመንገዱ አቅም እና ደረጃ ከገጠር መንገድነት በጣም ከፍ ያለ ሲሆን የመንገዱ አንደኛው ጫፍ አንገረብ ሆኖ የአይከልን (ጭልጋን) ወረዳው በቀጥታ ከትግራይ ክልል ጋር ለመገናኘት ያለመ መንገድ ነው፡፡ ምክንያቱም አንገረብ የሰሜን ጎንደርን በሰሜን ምዕራብ በኩል ከዳንሻ ጀምሮ እስከ አብደራፊ ድረስ ባለው ቦታ ከትግራይ ክልል ጋር የሚለየው ተፈጥሯዊ የወንዝ ድንበር በመሆኑ ነው፡፡
• ጭልጋ እና ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳዎች ከትግራይ ክልል ጋር ምንም አይነት የወሰንም ሆነ የሚጋሩት ድንበር የሌለ ከመሆኑም በላይ በትግራይና በሁለቱ ወረዳዎች መካከል የመተማ (ገንደ ውሃ) ወረዳ እና የላይ አርማጭሆ ወረዳ ይገኛሉ፡፡ ይህ ደግም በሁለቱ ወረዳዎች (ጭልጋ እና ምዕራብ አርማጭሆ) መካከል ከዚህ በፊት ምንም ዓይነት የጎንዮሽ የንግድ እና የህዝብ እንቅስቃሴ የሌለበት በመሆኑ የሚሰራው መንገድ ምንም ዓይነት ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፋይዳ የለውም፡፡
ባጭሩ የዚህ መንገድ ስራ ማለት ከአርባምንጭ ወደ ድሬዳዋ ለመሄድ በአዋሳ ዝዋይ አልፎ የሚሄደውን ትቶ የቀጥታ የጎንዮሽ መስመር ለመገንባት እንደ መሞከር ማለት ነው፡፡ ይህ ዓይነት ግንባታ ቢያንስ ለጊዜውም ቢሆን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ህዝቦቹ እና አካባቢዎች መገናኘት አለባቸው ከተባለ እንኳን አሁን በጥቅም ላይ ያለው መንገድ ተስተካክለውና ደረጃቸው ከፍ ተደርጎ ወደ ግልጋሎት እንዲገቡ ቢደረግ የህዝብን ፍላጎት በበቂ ሁኔታ ሟሟላት የሚቻልበትን ሁኔታን መፍጠር ይቻል ነበር፡፡ ከዚህ አይነት የቅንጦት መንገድ ይልቅ ለዘመናት በህዝብ የይሰራልን ጥያቄም ሆነ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸው ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያላቸው መንገዶች ነገር ግን በስርዓት ያልተሰሩ መንገዶች በክልሉም ሆነ በዞኑ ይገኛሉ፡፡ ለአብነት የሚከተሉትን እናንሳ፡
1. ከአብደራፊ (ምዕራባዊ አርማጭሆ) – ማር ዘነብ – ሶሮቃ – ሳንጃ (ታች አርማጭሆ) – ጎንደር የሚያገናኘው እና ከፍተኛ የሆነ የሰሊጥ፣ የማሽላ እና የጥጥ ምርት የሚጓጓዝበት መንገድ፡፡
2. ከገንደውሃ (ሸኸዲ) – ሽንፋ – ቋራ – አለፋ ጣቁሳ ያለው ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፋይዳ ያለው መንገድ እስካሁንም ድረስ በጣም አሮጌ የሆነ የጠጠር መንገድ ነው ያለው፡፡
3. ከገንደውሃ (ሸኸዲ) – ኮኪት – መሻህ – ፍልውሃ – እብርሃጅራ – አብደራፊ ያለው መንገድ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጥቅሙ ምንም እንኳን ከፍ ያለ ቢሆንም መንገዱ ወደ ጠጠር መንገድ እንኳን አላደገም፡፡
4. ከአለፋ – ጣቁሳ – አይከል ያለው መንገድ ከፍተኛ የግብርና ምርት እና የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች የሚመረቱበት አካባቢ ከመሆኑም በላይ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ከፍተኛ የሆነ መንገድ አልተሰራም፡፡
5. ከጎንደር – ቁስቋም – ሮቢት – ደራስጌ ማርያም – ምድራሮ ያለው ከእግር መንገድ የተሻለ አይደለም፡፡
6. ከጎንደር ማክሰኝት በለሳ – አርባያ – ጉሃላ . . . በ17 አመቱ የትግል ወቅት ከፍተኛ ግልጋሎት የሰጠ መንገድ ቢሆንም አሁን ግን ከነአካቴው የተረሳ መንገድ ነው፡፡
7. ከሀሙሲት – አርብ ገቢያ – አምበሳሜ – ገላውዲዎስ ያለው ጠቃሚ መንገድ በብዙ ችግሮች የታጠረ የጠጠር መንገድ ነው፡፡
8. ከባህርዳር – አንዳሳ – ጭስ አባይ … በቱሪዝም ዘርፉ ከክልልም ሆነ ለ አገሪቱ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝ መንገድ በጣም በአሳዛኝ ሁኔታ የወረደ የጠጠር መንገድ ነው ያለው፡፡
9. ከሸኸዲ – ኮኪት – ዳስ – በርሜል ያለው መንገድ ኢኮኖሚያው ጠቀሜታው ከፍተኛ ቢሆንም የእግር መንገድ ደረጃውን አለቀቀም፡፡
10. ከሽንፋ መንገድ ተገንጥሎ ወደ ማህበረስላሴ ገዳም የሚወስደው ከፍተኛ የሆነ የንግድ እንቅስቃሴ ያለበት አካባቢ እስካሁን የጠጠር መንገድ እንኳን የለውም፡፡
እና ሌሎች የጠጠር መንገድነት እንኳን እድል ያላገኙ ነገር ግን ቅድሚያ ተሰጥቶ መሰራት ያለባቸው እና ለዘመናት ህዝብ እስካሁንም ድረስ እየተማረረባቸው ያሉ መንገዶች አሉ፡፡ ስለዚህ ይሄን መንገድ ለምን መሥራት አስፈለገ? ለምንስ አሁን እዲሆን ተደረገ? እና ተያየዝ ጥያቄዎች መመለስ ይኖርብናል፡፡
ባጭሩ የጭልጋ ወረዳ የቅማንት ማህበረሰብ በስፋት የሚገኝበት አካባቢ ነው፡፡ የቅማንት ማህበረሰብ የማንነት ጥያቄ አንስቶ በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ ውጥረት ተከስቶ እንደነበርና ህይዎት እና ንብረት የጠፋባቸው የቅርብ ጊዜ ክስተቶች እንደነበሩ የሚታወስ ነው፡፡ ይህንን ክስተት ደሞ ህወሓት/ኢህአዴግ የዐማራውን አንድነት ለመሸርሸር እና ለማዳከም እየተጠቀመበት እንደሚገኝ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ማስረጃ መጥቀስ ካስፈለገም ጉዳዩን ባስተባባሪነት የያዙት ግለሰቦች በህወሓት ጋባዥነት መቀሌ ድረስ በመሄድ ስልጠና እና የገንዘብ ድጋፍ የተሰጣቸው መሆናቸው እና የቅማንት የማንነት ጉዳይ ከቅማንት ማህበረሰብ በበለጠ ሁኔታ ህወሓትና የትግራይ ልሂቃን ሲያጮሁትና ሲያራግቡት መገኘታቸው ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ሊሰራ ከታሰበው መንገድ ጀርባ ህወሓት ሰይጣናዊ የሆነ ስውር ሴራ እንዳላት መረዳት እንችላለን ማለት ነው፡፡ ይሄም የቅማንት ማህበረሰብን ቀጥታ ከትግራይ ጋር በማገናኘት መጀመሪያ የዐማራውን እንድነት እና ህብረት ማፈራረስ ሲሆን ሲቀጥል ደግሞ አይን ያወጣ ምዕራባዊ ዐማራን ገንጥሎ ውስዶ ከቤንሻንጉል ጋር በማገናኘት እና ወደ ትግራይ በመጠቅለል ታላቋን የትግራይ ሪፐብሊክን ለመመስረት የሚያደርገው የሞት ሽረት ጥረት አካል መደገፍ ነው፡፡ በተጨማሪም አካባቢውን ከትግራይ አየተነሱ በዘላቂነት ለማተራመስ እና ልዩነቶች እንዲሰፉ ለማድረግ የታለመበት መንገድ መሆኑ ነው፡፡ በምስሉ ላይ ለመመልከት እንደሚቻለው አሁን በጭልጋ እና መተማ እንዲሁም ጎንደር ያለው የመንገድ መረብ ከበቂ በላይ መሆኑ ብቻ ሳይሆን አላስፈላጊም ጭምር ነው (በቀይ የተሰመረው መስመር አሁን ሊሰራ የታሰበው መንገድ ነው)፡፡ ከዛ ይልቅ በሙስና ምክንያት ሳይመረቅ ጀምሮ የተበላሸውን የጎንደር – ጭልጋ – መተማ – ሱዳን መንገድ በማደስ ደረጃውን ማስተካከል እና ከፍ ማድረግ ጊዜ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መንገዱ ሊገነባበት የታቀደበት የአካባቢው ተፈጥሯዊ መልከዓምድር የታቀደውን ዓይነት መንገድ ያውም በሱር ኮንስትራክሽን አቅመቢስነት ለመገንባት ከአስቸጋሪም በላይ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ጉዳዩን ተገን በማድረግ በተለመደ ዘይቤያቸው ለክልሉ የተመደበለትን የመሰረተ ልማት በጀት በተለያየ መንገድ ወደ ትግራይ ክልል ለማጋዝ የታለመ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ስለዚህ ይህ በዘርፈ ብዙ ሴራ የተተበተበው መሰረተ ልማት ከአሁኑ እንዲቆም እና እንዲቀር ሁሉም ያገባኛል የሚል አካል በሚችለው እና በአለው አቅም መተባበር ግድ ይላል፡፡ ሰላም!!

No comments:

Post a Comment

wanted officials