Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, October 31, 2016

ሰበር ዜና:-አፍሪካ ህብረት ወታደራዊ ደህንነት ህወሃት ላይ ቅሬታዉን እያሰማ ይገኛል !



ልሁል አለም
ያሳለፍነዉ እሮብ ነበር የሶማሌያዉ አል ሸባብ በደቡብ ሶማሌያ የምትገኘዉን ቲየግሎው Tiyeeglow የተባለችዉን ከተማ መቆጣጠሩን ይፋ ያደረገዉ ባኮንና ሂራን የተባሉ ቅርብ የሆኑ ቁልፍ ክልሎችን ለማጥቃት የሚመቸዉ ሲሆን ይህን አል ሸባብ ሄልጋን የሚገኘዉን የአሚሶም ወታደራዊ ጣቢያን በመቆጣጠር የበላይነቱን ተቆጣጥሯል።
የአፍሪካ ህብረቱ ሰራዊት ከፍተኛ መሰዋትነት ከፍለዉ ሞተዉና ቆስለዉ ያስከበሩትን የጦር ቀጠናዎች የኢትዮጵያ መከላከያ ሆን ብሎ ለአልሸባብ አስረክቦ ሊወጣ የቻለበት ምክንያት እንዲጣራ የሲ አይ ኤ መረጃዎች ለህብረቱ ወታደራዊ መኮንኖች መተላለፉን ዛሬ ከህወሃት ወታደራዊ ደህንነት ምንጮች ለማወቅ ተችሏል።
የአልሸባብ የወታደራዊ ድርጊቶች አፈ ቀላጤ አብዲአሲስ አቡ ሙሳብ ” የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊቶች የጦር ቀጠናዎቹን ለቀዉ እንደወጡ በእግራቸዉ ተክተናል በማለት ያረጋገጠ ሲሆን አብዱአሲስ አያይዞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አል_ኢሊ ከተማን በጥር 11 ሄልጋንን ደግሞ በጥር 23 የለቀቀ ሲሆን በተለይ የመከላከያ ሰራዊቱ ሄልጋንን ለመልቀቅ ባኮበኮቡበት ሁኔታ ላይ ደርሰን በከፈትነዉ ተኩስ መጠነኛ ጉዳት አድርሰናል ”
በማለት የገለጸ ሲሆን ከአብዱአሲስ ፍንጭ እና ከሌሎች በተሰበሰበ ማስረጃ ምክንያት በአልሸባብና በህወሃት መካከል የመረጃ ልዉዉጥ መኖሩን አመላክቷል በማለት የደመደሙት የህብረቱ መኮንኖች ለህወሃት የሐይል ቡድን አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
የህብረቱ ከፍተኛ መኮንኖች በቅርቡ በአዲስ አበባ ላይ በሚደረገዉ የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ህወሃት ቡድን ማብራሪያ እንዲሰጥ ለማድረግ እየጣሩ ይገኛሉ
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
weyane-leba
    


No comments:

Post a Comment

wanted officials