Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, October 14, 2016

በደቡብ ክልል በጌዴኦ ዞን በተፈጠረ ግጭት ከ25ሺህ በላይ ነዋሪ ወደ ቤተክርስቲያናት ተጠግቷል



በዲላ፡ ይርጋጨፌ፡ ወናጎ፡ ፍሰሀገነት፡ ገደብ እና በሌሎች የጌዲኦ አከባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ከ25ሺህ በላይ ነዋሪ ወደ ቤተክርስቲያናት ተጠግቷል። ህዝቡ የድረሱልን ጥሪ አቅርቧል።በደቡብ ክልል በጌዴኦ ዞን ካለፈው አርብ ጀምሮ በገዢው ስርዓት ሆን ተብሎ በተቀነባበረው ጥቃት መንግስት 23 ሰዎች መሞታቸውን ቢገልጽም ትክክለኛው አኃዝ ከዚህ በብዙ እጥፍ የሚበልጥ እንደሆነ ነዋሪዎች እየገለጹ ናቸው። መንግስት በኢሬቻ በዓልም ሰባት መቶ ያህል ሰው ተገድሎ 55 ብቻ ማለቱ ይታወቃል። የቀጥሩ ነገር ይቆይና በአካባቢው የተፈጠረው ነገር ያሳምማል። ሰርተው ጥረው ግረው ለብዙዎቹ ከተሞች ውበት የፈጠሩ ነጋዴዎች ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎ በየእምነት ቤቱ የተጠለሉ ሲሆን በምግብ እጦትና ውኃ ጥም እየተሰቃዩና የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው። ችግሩ ከተፈጠረ አንድ ሳምንት እየተጠጋው ቢሆንም እስካሁን ተፈናቃዮችን እንዴት ናችሁ ብሎ ያናገራቸው አንድም አካል የለም። በአማራ ክልል የሚኖሩ የትግራይ ብሄረሰቦች ተፈናቀሉ ተብሎ ያ ሁሉ አቡዋራ ሲጨስ ባየን ማግስት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሞተውና በአስር ሺዎች ተፈናቅለው እንደጉዳይ የማይታዩ መሆኑን እየተገነዘብን ነው። ለምን ቢባል የወርቁ ዘር አይደሉማ። ለምን ቢባል በህወሀት መራሹ ስርዓት እንዲጠፉና መቀጣጫ እንዲሆኑ የሚፈለጉ ህዝቦች ናቸውና። ይህን እውነት ነው እንግዲህ የአንድ ብሄር የበላይነትና የአንድ ፓርቲ የበላይነት የለም ብለው አይናቸውን አጥበው የሚከራከሩን።
ብቻ ለሁሉም ጊዜ አለው። የወያኔም ስርዓት ግብአተ መሬት የሚፈጸምበት ጊዜ ሩቅ አይደለም።


ሞት ለከፋፋዩ ወያኔ!

No comments:

Post a Comment

wanted officials