Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, October 8, 2016

አየር ኃይልና ሕዝባዊ እምቢተኝነት



ሕዝብ ሲቆስል የሚቆስለው ፣ ሕዝብ ሲደማ የሚደማው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከስርዓቱ ጋር አብሮ የተቀየረ ይመስላል ። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በስርዓቱ አየር ኃይል ውስጥ እያገለገሉ የነበሩት ወጣት በራሪ የህዝብ ልጆች አሰላለፋቸውን በፍጥነት ከህዝብ ጋር ማድረጋቸው የሚታወቅ ነው ። እነዚህ ወጣት በራሪዎች በህዝባቸው ላይ የሚደረገውን እልቂት ባሉበት ቦታ ሁሉ ሆነው በዝምታ የሚመለከቱት አይሆንም ።United Former Ethiopian Air Force Association
በሌላ በኩል ደግሞ በአሁኑ ሰዓት ያለው የህውሃት አየር ኃይል የአገር ተወላጆችን ወደ ጐን ትቶ በቅጥረኛ በራሪዎች መመካት መጀመሩ ውሎ አድሯል ። ይህ አካሄድ “ለምን” ብሎ የሚጠይቅ ባለቤትነት የሚሰማው ዜጋ እንዳይፈጠር ታቅዶ የተሰራ ነው ። በትጥቅ ትግል የታገዘ ህዝባዊ እምቢተኝነትን ለማፈን ይረዳ ዘንድ የአንድ መንደር ልጆችን በሄሊኰፕተር ስኳድሮን ውስጥ አጭቆ በገሃድ እየተፈፀመ ያለውን የሰላማዊ ሕዝብ ፍጅት በአየርም ሲያስፈራራበትና ሲያሸብር ይታያል ።
ዛሬ ዛሬ ተዋጊ አውሮፕላኖቹ በራሪ አጥተው ሰንበሌጥ እየበቀለባቸው ይገኛሉ ። ጥቂት የትግራይ ተወላጅ ተለማማጅ በራሪዎች ብቻ ተመርጠው የተሰገሰጉበት ስኳድሮን አልፎ አልፎ ከባዕድ ዜጐችና በተጨማሪም ኢትዮጵያም የራስዋን ዜግነት ከመረቀችላቸው የሩስያ በራሪዎች ጋር የልምምድ በረራ ያደርጋሉ ። ይህ አካሄድ ወደድንም ጠላንም ከትግራይ ውጪ ያለውን ዜጋ ሁሉ የሚያሳስበውና ለወደፊቱም ለጥቃት እንደሚያጋልጠው ይገባናል።
ለዚህም ነው ኦክቶበር 9 ቀን 2016 ዓም የእሬቻን ሃይማኖታዊ በዓሉን በሚያከብረው ህዝባችን ላይ ከአየር ኃይሉ ባህል ውጪ ፍፁም ዘግናኝ ፍጅት የተፈፀመው ። ይህንን ድርጊት በመፈፀምና በማስፈፀም ቀጥተኛ ተባባሪ የሆኑት የሄሊኰፕተር ስኳድሮን አባላት በኃላፊነት ያስጠይቃቸዋል ። የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አለም ዓቀፍ ህብረት በየጊዜው ያለማቋረጥ በህዝባችን ላይ እየተፈፀመ ያለውን የጅምላ ፍጅት ደግሞ ደጋግሞ እያወገዘ የህውሃት አየር ኃይል እያደረገ ያለውን የሰላማዊ ህዝብ ፍጅት በኃላፊነት ይጠይቃል ።
በዚህም መሰረት
airforce-table1
እና የመሳሰሉት ከተጠያቂነት እንደማይተርፉ እናሳውቃለን ።
UFEAFA (United Former Ethiopian Air Force Association)
www.formerethiopianairforce.com

No comments:

Post a Comment

wanted officials