-----------------------------------------
የቀድሞ አንድነት አባል ስንታየሁ ቸኮል ዛሬ ጥቅምት 10/2009 ዓ.ም ከሰአት በአራዳ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለሶስተኛ ጊዜ ቀረበ።
በፀረ-ሽብር አዋጁ ክስ የቀረበበት ስንታየሁ ቸኮል፣ በታሰረበት የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመበት እንዳለ ለፍ/ቤቱ አስረድቷል። በታሰረበት ክፍል ውስጥ በፌስታል እንዲፀዳዳ እየተደረገ እንዳለ፣ ድብደባ እንደደረሰበት፣ በ28 ቀን ውስጥ ለአንድ ቀን ብቻ ወጥቶ እንዲናፈስ መደረጉንና በጨለማ ክፍል ውስጥ መታሰሩን ተናግሯል። ተቋሙን በመወከል ፍ/ቤት የቀረበው መርማሪ እንደዚህ ያለ ተግባር እንዳልፈፀመ የተናገረ ሲሆን፤ ስንታየሁም ተቋሙ ነው ድርጊቱን እየፈፀመ ያለው ሲል ለፍ/ቤቱ አስረድቷል። ፍ/ቤቱ ተቋሙ ላይ የቀረበውን ቅሬታ ተቋሙ ቀርቦ መልስ እንዲሰጥበት አዟል።
ፖሊስ ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለመሰብሰብ እንዲሁም የሚተረጎሙ ፅሁፎችን አስተርጎሜ ለማቅረብ ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ብሎ በጠየቀው መሰረት፣ ፖሊስ የጠየቀውን የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ተለዋጭ ቀጠሮ ለህዳር 8/2009 ዓ.ም ሰጥቷል።
ፍትህ
No comments:
Post a Comment