የጀርመኗ መራሔ መንግስት የኢህአዴግን ፓርላማ ተጠየፉ::
BBN news
ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች ሁለት የአፍሪካ ሀገራትን የሚጎበኙት የጀርመን መራሔተ መንግስት አንገላ መርከል፣ በኢህአዴግ ፓርላማ ተገኝተው ንግግር እንደማያደርጉ ተገለጸ፡፡ ቻንስለሯ በኢትዮጵያ ጉብኝታው በፓርላማ ተገኝተው ንግግር የማያደርጉት፣ ፓርላው መቶ ፐርሰንት በኢህአዴግ አባላት የተሞላ በመሆኑ እንደሆነ ለስርዓቱ ቅርበት ያለው ሪፖርተር ጋዜጣ ገልጿል፡፡
የህወሓት መንግስት መራሔተ መንግስቷ በፓርላማ ተገኝተው ንግግር እንዲያደርጉ ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም፣ አንገላ መርከል ግን ‹‹በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ስር በዋለ ፓርላማ ውስጥ ንግግር ማድረግ ምንም ለውጥ አያመጣም›› በማለት የኢህአዴግን ፓርላማ ተጠይፈውታል፡፡ ቻንስለር አንገላ መርከል በኢትዮጵያ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የመንግስት ወታደሮች በንጹኃን ዜጎች ላይ የሚወስዱትን የኃይል እርምጃ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር የሚወያዩ ሲሆን፣ በኢህአዴግ አምባገነናዊ መዳፍ ስር ስለወደቀው የተቃውሞ ፖለቲካ ጉዳይ ከመንግስት ጋር እንደሚወያዩም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ይገባሉ ተብለው የሚጠበቁት ቻንስለር መርከል መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገውን የአፍሪካ ህብረት የሚጎበኙ ሲሆን፣ የየሀገራቱ ተወካዮችንም ያወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በኢህአዴግ መሪዎች እና ካድሬዎች የተሞላውን የሀገሪቱን ፓርላማ የተጠየፉት መርከል፣ ከተመረጡ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጋር በጀርመን ኤምባሲ የሚወያዩ ሲሆን፣ በጀርመን ኤምባሲ አማካይነት ከተመረጡ የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋርም ውይይት እንደሚኖራቸው መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያን ከጎበኙ የዓለም መሪዎች መካከል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፣ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ የደቡብ ኮርያዋ ፕሬዚዳንት ፓርክ ጉዊን፣ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ የሚጠቀሱ ሲሆን፣ ከነዚህ መሪዎች ውስጥ አንዱም ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር አለመወያየታቸውን ከተገኘው መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ቻንስለር አንገላ መርከል ከኢትዮጵያ አስቀድሞ ማሊ እና ኒጀርን ጎብኝተዋል፡፡

No comments:
Post a Comment