ወደ አማራ ክልል እንዲንቀሳቀስ የታዘዘው ጦር ማብራሪያ ጠየቀ።
ሚኒልክ ሳልሳዊ
የምስራቅ እዝ ወታደራዊ ደህንነት ምንጮች እንደገለጹት ከእዙ የተለያዩ ቡድኖች ተዋቅረው የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጁን ለመተግበር ወደ ኣማራ ክልል እንዲንቀሳቀሱ የታዘዙ ወታደሮች ማብራሪያ መጠየቃቸውን ጠቁመዋል። የኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጁ ከሕዝቡና ከሕገመንግስቱ ኣንጻር ያለውን ሃገራዊ እደምታ በተመለከተ እንዲሁም የግጭት ኣፈታትን በተመለከተ ከሕዝብ ጋር መወያየትን ያጣመረ ስራ ስለመሰራቱ ማብራሪያ እንዲደረግላቸው መጠየቃቸው ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል።ከጦር ሃይሎች ጠቅላይ መምሪያ በተላከ መመሪያ መሰረት በጎንደር በመተማ በባህርዳር በደብረማርቆስና በመተከል ያሉትን የወያኔ ኣግዓዚ ወታደሮች እንዲረዱ የታዘዙት የምስራቅ እዝ ወታደሮች ማብራሪያ መጠየቃቸውን ተከትሎ በዚህ ሳምንት ከመከላከያ ሚኒስቴር ኣንድ ቡድን ወደ ምስራቅ እዝ ይዘልቃል ተብሎ ይጠባቃል ሲሉ ወታደራዊ ደህንነቶች ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል።
በምስራቅ እዝ ያሉ ወታደሮችን ወደ ኣማራ ክልል ወስዶ በምትካቸው በምስራቅ በኩል ከሶማሊያ የሚመለሰውን ጦር ለማስፈር ያቀደው ወያኔ በወታደሮች እምቢተኝነት ጉዳዩ የዘገየበት ሲሆን ከሶማሊያ የተመለሱ ወታደሮችን በኣማራና ኦሮሚያ ክልል ለማስፈር ያሰበው እቅድን ያጠፈው የሰላም ኣስከባሪ ሃይሎች የሚላቸውን እና ስለ ወቅታዊ የትዮጵያ ጉዳይ በቂ መረጃ ያላቸውን ወታደሮች ሌላ ጥያቄ ስለሚያነሱ በሂደት ኣስፈላጊውን ለማከናውን ትልም የነደፈ ሲሆን ኣብዛኛዎቹ የትግራይ ተወላጆች ከሶማሊያ እየተመለሱ በኣማራ ክልል ያለውን የኣግዓዚን ገዳይ ጦር መቀላቅላቸውም ምንጮቹ ገልጸዋል።
No comments:
Post a Comment