Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, October 20, 2016

በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ዉስጥ የሚገኘዉ ህወሃት ለሐይማኖት አባቶች የመጨረሻ ጥሪ አስተላልፏል “”” አድኑኝ “””

ሰበር ዜና ! ! ! በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ዉስጥ የሚገኘዉ ህወሃት ለሐይማኖት አባቶች የመጨረሻ ጥሪ አስተላልፏል “”” አድኑኝ “””! !



ህዝባዊ አመጹ ህወሃትን እያሽመደመደው ለመሆኑ መረጃዎች ብሐራዊ አገልግሎት ዉስጥ ከሚገኙ የዉስጥ አርበኛ ወገኖቻችን እየደረሰን ይገኛል።
የህወሃት የጎጥ ቡድን ለኢትዮጵያ የኦሮዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ሲኖዶስ ተጠሪ አቡነ ማትያስ እንዲሁም ለእስልምና ጉዳዮች ተጠሪ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ተንተርሶ ህዝቡን እንዲያስተምሩ እንዲገስጹና እንዲመክሩ በተለይም በቤ/ክርስቲያንና በመስኪዶች አካባቢ በሚደረጉ እለታዊ እና ሳምንታዊ እንዲሁም ወርሐዊ በአላት ላይ ምንም አይነት አመጽ ቢነሳ እርምጃ እንደሚወሰድ የሕይማኖት አባቶች ህዝቡን እንዲያስጠነቅቁ እንዲያስፈራሩ መመሪያ ልኳል።
ህወሃት የሐይማኖት ተቋማት የአቸኵይ ግዜ አዋጁ ቀኝ እጅ እንዲሆኑ ጥሪ ማስተላለፉን ተከትሎ አቡነ ማትያስ በሐገር ዉስጥና በዉጭ የሚኖሩ ጥሩ የመስበክ ችሎታ አላቸዉ የተባሉ ቀሳዉስትንና አባቶችን ወደ አዲስ አበባ ጠርተዋል።
በመሆኑም ይህንን የአቡነ ማትያስን ጥሪ በመቀበል በተለያየ ሐገር የሚኖሩ አባቶች የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር ወደ አዲስ አበባ እየተመሙ ሲሆን የደቡብ አፍሪካ የብሉም ፎንቴን ኪዳነ ምህረት አባት አባ ገ/ማርያም በ /16/10/2016 የደርሳቸዉን ጥሪ ተከትሎ ዉስጥ ዉስጡን ጫና መፈጠሩን ከታማኝ ምንጮች ስናረጋግጥ አቡነ ማትያስ በተለይም ከገር ዉስጥ ከተጠሩ የሐይማኖት አባቶች ማጉረምረም የተነሳ ከፍተኛ ተቃዉሞ ይደርስባቸዋል የሚል ግምትም ሐይማኖታዊ ተሳትፎዎችን ችግር ዉስጥ ከቷቸዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

No comments:

Post a Comment

wanted officials