በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት አስመልክቶ የእስራኤል መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስራኤላዊያን ወደ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ከሚያደርጓቸው ጉዞዎች እንዲታቀቡ አሳሰበ። የውጭጉዳይ ሚንስተር መስሪያ ቤቱ ከሁለቱ ክልሎች በተጨማሪም በኤርትራ፣ በሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ኬኒያ ድንበር አስር ኪሎሜትሮች በሚገኙ አካባቢዎች እንዳይሄዱ አስጠንቅቋል።
በኦሮሚያ ክልል በቢሾፍቱ የተፈጸመውን እልቂት ተከትሎ በአካባቢው ሰላም በመደፍረሱ ዜጎቹ እንዳይጓዙ ጥሪውን አቅርቧል። የእስራኤል መንግስት አስቀድሞ በአማራ ክልል ከተሞች በተለይ በጎንደር፣ ባህርዳርና ደብረታቦር እገዳ መጣሉ ይታወሳል። በእሁዱ የኢሬቻ በዓል ላይ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተተኮሱት አስለቃሽ ጋዞች ለዜጎች ተረጋግጦ መሞት መንስኤ መሆናቸውን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ ነጻነታቸውን ጠያቂ ዜጎች ከጊዜወደጊዜ እያደገ መምጣቱን እና ቀጠናው ከምስራቅ አፍሪካ አስጊ እየሆነ መምጣቱንም ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አትቷል። የኢትዮጵያ መንግስት የምእራብ ሃገራት አጋር ቢሆንም የኢንተርኔት አገልግሎቶቹን ማቋረጡ፤ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚወስደው ኢሰብዓዊ እርምጃዎች አሜሪካንን ጨምሮ ከአጋር አገራት ማውገዛቸውን ዘታይም ኦፍ ኢዝራኤል ዘግቧል።
No comments:
Post a Comment